የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

Nov 28, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ ሕዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን ቁልፍ የትኩረት መስኮች ባማከለ መልኩ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ።

የአፍሪካ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በሞሮኮ ራባት ተካሄዷል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከፎረሙ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የበጀት ድጋፍን ማጠናከር፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በሌሎች ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የተቀናጀ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር ማድረግ እና ኢትዮጵያ የምታዘጋጀውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በፋይናንስ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ያላቸው የቆየ አጋርነትም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ባንኩ ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች እየተወጣ ያለውን ወሳኝ ሚናም አንስተዋል።

ባንኩ የኢትዮጵያን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት አድንቀዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የሪፎርም ሂደት ያደነቁ ሲሆን ባንኩ በኢትዮጵያ የግል ኢንቨስትመንትን በሚያሳድጉ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት በሚፈጥሩ መስኮች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ እና የባንኩ ፕሬዝዳንት በውይይቱ ላይ ተከታታይና የቴክኒክ ምክክሮችን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን በዘላቂ ልማት፣ ቀጣናዊ ትስስር እና የግሉ ዘርፍ እድገት በሚያጠናክር መልኩ ለማጎልበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026