🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዲጂታል ግብርናን ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ገለጹ፡፡
የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው የዲጂታል ግብርና ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ጉባኤው “ኢኖቬሽን እና የዲጂታል መፍትሄዎችን ለግብርና ዘርፍ በመጠቀም የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ ብሩህ ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ኅብረቱ ዲጂታላይዜሽንን የልማት አጀንዳው አድርጎ እየሰራ ነው።
የግብርናው ዘርፍም በዚህ የዲጅታላይዜሽን አህጉራዊ ስትራቴጂ ውስጥ ትኩረት እንደተሰጠው አንስተዋል።
ኮሚሽኑ አባል ሀገራት ለዲጂታል ግብርና የመረጃ አጠቃቀምና አስተዳደር አመቺ ፖሊሲዎችን እንዲያዘጋጁ እና እንዲተገብሩ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ለአርሶ አደሮች፣ ለግብርና ባለሙያዎችና ለወጣቶች በዲጂታል ክህሎቶች ዙሪያ ሥልጠና እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል።
በአፍሪካ ዲጂታል ግብርናን እውን ለማድረግ የአባል ሀገራት መንግስታት፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች እና የምርምር ተቋማት በቅንጅት እንድሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በበኩላቸው የአፍሪካን የግብርና ሥርዓት ለመለወጥ እና የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ዲጂታል ግብርናን መተግበር የግድ ነው ብለዋል።
ዲጂታል ግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የምርት ብክነትን ለመቀነስ፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነትን ለማስፋት እንዲሁም የመቋቋም አቅምን ለመገንባት ቁልፍ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ወጣቶች የአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ለኢኖቬሽንና ለዲጂታል ግብርና ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት ዲጂታል ግብርናን እንደ ቁልፍ ስልት ወስዳለች።
መንግስት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘርፉን ለማዘመን የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን በስማርት ስልኮች አማካይነት ተደራሽ ማድረግ፣ ትክክለኛ የግብርና መረጃዎችን በአንድ ቋት መያዝና ማዘመን ላይ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የግብርና ግብዓትን ተደራሽ ማድረግ፣ ከማሳ እስከ ገበያ ባለው ሂደት ውስጥ ያሉ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማጎልበት ዲጅታላይዜሽን ላይ መሰራቱን ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026