🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት በማሳለጥ የጎላ ሚና እንዳለው የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።
ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን መፃኢ የፋይናንስ ስርዓት የሚያሳልጥ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።
ኢትዮጵያ አካታች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል።
ማሻሻያው ወደ ተሟላ ትግበራ ከገባ ወዲህ ማክሮ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ሁሉን አቀፍ ዕድገት ማረጋገጥ በሚያስችል ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሀገር ውስጥ ገቢን በማስፋት ዕምርታዊ ለውጥ መመዝገቡንም ገልጸዋል።
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ሪፎርም መደረጉን ገልጸው፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያሳድግ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
በኢኮኖሚ ሪፎርሙ መሰረት ወደ ሥራ የገባው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት በማሳለጥ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ ተዓማኒ፣ እውነተኛና ተስማሚ የፋይናንስ ምህዳር ለመፍጠር በተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር ይገባል ብለዋል።
በአግባቡ የተደራጀ እና የተሟላ መሰረተ ልማት ያለው የካፒታል ገበያ ስርዓት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሳደግና ከዓለም የፋይናንስ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር ያግዛል ብለዋል።
ይኸውም የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለኢንቨስተሮች መተማመኛ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026