🔇Unmute
ባሕርዳር ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የቅዳሜና እሀድን ጨምሮ የተለያዩ የገበያ አማራጮች በመስፋፋታቸው ገበያን በማረጋጋት ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ኢብራሂም መሀመድ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት፤ ሕገወጥ ንግድን በመከላከል ገበያ የማረጋጋቱ ተግባር በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህም በስምንት ከተሞች የተገነቡ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላትን ወደ ስራ በማስገባት፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያን በማስፋት ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለሸማቹ ሕብረተሰብ በቀጥታ እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
እየቀረበ ያለውም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከአንድ ቢሊዮን 270 ሚሊዮን ብር በላይ ተዘዋዋሪ ብድር ለሸማች ሕብረት ስራ ማሕበራትና ለዩኒየኖች በማመቻቸት እንደሆነ አስረድተዋል።
በየከተሞቹ የተገነቡት የገበያ ማዕከላትም አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በተከናወነው ስራም የግብርና ምርት ዋጋ በየጊዜው እየቀነሰና ገበያው እየተረጋጋ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ይህም የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ስምንት ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ማቅረብ መቻሉንም አንስተዋል።
ገበያን ለማረጋጋት እየተደረገ ካለው ተግባር ጎን ለጎንም መንግስት ለሠራተኛው ያደረገውን የደመወዝ ጭማሪ ተከትሎ ምርትን በሕገወጥ መንገድ በደበቁ 308 ድርጅቶችና የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ በተገኙ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱንም ጠቅሰዋል።
በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 117 ሺህ ሊትር ነዳጅ መያዙንም አረጋግጠዋል።
ለዋጋ ጭማሬ ምክንያት የነበሩና በተለያዩ ከተሞች ተቋቁመው ቀረጥ ያስከፍሉ የነበሩ ኬላዎች እንዲነሱ መደረጉን ጠቅሰው፤ ተግባሩን ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ሕገወጥ ንግድን በተቀናጀና በተናበበ አግባብ በመከላከልና በመቆጣጠር ጤናማ የግብይት ስርዓት እንዲፈጠር የክትትልና ቁጥጥር ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢሮው ኃላፊ ኢብራሂም መሀመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026