🔇Unmute
ዲላ ፤ታህሳስ 2/2018 (ኢዜአ)፡-በዲላ ከተማ እየተገነባ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።
የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በከተማው በሁለተኛ ምዕራፍ እየተከናወነ ያለው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተፋጠነ መሆኑን አስታውቋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የዲላ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ካጎናጸፋት ውበት ባለፈ ዜጎች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች እንዲሰማሩ የሥራ እድል እየፈጠረ ነው።
በከተማው በአትክልት ንግድ ሥራ የተሰማሩት ወይዘሮ ትግስት ታምራት እንዳሉት የኮሪደር ልማቱ ጽዱ አካባቢዎች መፍጠር እንደቻለ ተናግረዋል።
ይህም የከተማዋን የጽዳትና የውበት ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ እሳቸውም የንግድ ሥራቸውን ንጹህና ጽዱ በሆነ አካባቢ ለማከናወን እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው ቀደም ሲል ለእይታ የማይስቡና ቆሻሻ መጣያ ጭምር የነበሩ ስፍራዎችን ወደ መዝናኛነት የቀየረ መሆኑን ያነሱት ደግሞ ሌላዋ አስተያየት ሰጭ ወይዘሮ መሰረት አበበ ናቸው።
ልማቱ የከተማዋን ገጽታ እንዲቀየር ከማድረግ ባለፈ ለዜጎች የሥራ እድል እየፈጠረ መምጣቱን ገልጸው፣ በርካታ ሰዎች በኮሪደር በለሙ አካባቢዎች የንግድ ሥራ ጀምረው ገቢ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።
ለልማቱ መሳካት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዋ የተለወጡ አካባቢዎችን የመጠበቅና አረንጓዴ ስፍራዎችን የመንከባከብ ሥራ እንደሚያከናወኑም ተናግረዋል።
የዲላ ከተማ ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት በከተማው በመጀመሪያ ምዕራፍ የተከናወነው የ11 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት የከተማዋን ደረጃ በማሻሻል ለኑሮና ኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል።
በሁለተኛው ምዕራፍም ከተሽከርካሪና እግረኛ መንገድ በተጨማሪ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ የአረንጋዴ ልማት እንዲሁም መዝናኛ ቦታዎችን ያካተተ 10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ስራ እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል።
ልማቱ በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ከንቲባው፣ በተለይ የከተማው ነዋሪ ይዞታውን በመልቀቅና ግብዓት በማቅረብ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲጠቅል አስገንዝበዋል።
የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታና ውበት ከመቀየር ባለፈ ለዜጎችም የሥራ እድል እየፈጠረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በኮሪደር ለለሙ አካባቢዎች አስፈላጊውን ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026