የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኢንስቲትዩቱ ስራ መጀመር ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ሚናው የጎላ ነው

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ስራ መጀመር ዘመናዊና አስተማማኝ የፋይናንስ ስርዓት በመገንባት ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ለተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ስያሜ ይፋ የማድረግና የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።


በመድረኩ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የኢንስቲትዩቱ ወደ ስራ መግባት የፋይናንስ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽንን ለማሳለጥ ወሳኝ ነው።

በተጨማሪም ለፋይናንስ ስርዓቱ የጀርባ አጥንት ከመሆን ባለፈ አስተማማኝ የፋይናንስ ዘርፍ እንዲፈጠር፣ ህብረተሰቡ ስለፋይናንስ ዘርፉ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው እና ለውሳኔ ሰጪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት።

ይህም የኢኮኖሚ ዕድገትና ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።

ካሁን ቀደም የሂሳብ ባለሙያዎች ማረጋገጫ የሚቀበሉት ከውጭ ተቋማት መሆኑን በማውሳት፥ በይፋ ስራ የጀመረው የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ይህንኑ ተግባር በሀገር ውስጥ ማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ በተቋማት አሠራር ግልፅነትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የሂሳብ አያያዝ፣ ኦዲት እና የፋይናንሺያል ሪፖርት መረጃዎችን የማስተዋወቅ እና የማሳደግ አላማ እንዳለውም ጠቅሰዋል።


ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በየዓመቱ በርካታ የሂሳብ ባለሙያዎች የሚመረቁ ቢሆንም በኢትዮጵያ ያሉት የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር ግን በጣም አነስተኛ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የባለሙያዎችን ብቃት በማረጋገጥ ይህንኑ ችግር እንደሚፈታ የታመነበት ኢንስቲትዩት ዛሬ ሥራውን በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የዓለም ባንክ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026