የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በከተሞች ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

Jan 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና ፤ ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ) ፡- በከተሞች ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላከተ፡፡

የቢሮ ኃላፊዎቹ እንደገለፁት፤ በከተሞች ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማደራጀት ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው፡፡

የመደመር መንግሥት እይታን በመተግበር ዜጎች ባሉበት ሆነው በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ስማርት ከተሞችን መፍጠር ላይ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም በክልሉ ዘጠኝ ከተሞች የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ፈጣንና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በቀጣይም ተግባሩን በማስፋት በ15 ከተሞች ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የሲዳማ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ሰለሞን በበኩላቸው በከተሞች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ይነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተግባራዊ መደረጉን አንስተዋል።

በተለይም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ብልሹ አሰራሮችን ለማረምና የተገልጋይ እርካታን ለመጨመር መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡

አገልግሎቱን ለማስፋትም የመቶ ቀናት እቅድ መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ የመንግሥት አገልግሎትን የተቀላጠፈ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሰመራ ከተማ መጀመሩን የገለፁት ደግሞ የአፋር ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ጎቦኦ መሀመድ ናቸው።


በዚህም ቀደም ሲል በከተማ አገልግሎት አሰጣጥ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቀነስ መቻሉን አንስተዋል።

አገልግሎቱን በማስፋትም በክልሉ አዋሽን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ተደራሽ በማድረግ ተገልጋዩን ለማርካት መታቀዱን ገልፀዋል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው መንግሥት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሪፎርሞች መተግበሩን ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ መዘመንም የማህበረሰቡን እንግልት ለመቅረፍ የተጀመረዉ ጥረት አካል መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህም በዲጂታል የታገዘ አገልግሎትን እስከ ቀበሌ መዋቅር በማስፋት በዘርፉ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የገጠር ትራንስፎርሜሽንን መሰረት ያደረገ ሀገራዊ የንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ማካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026