🔇Unmute
ጂንካ፥ታህሳስ 28/2018(ኢዜአ) :- በጂንካ ከተማ የበዓል ገበያ የዕርድ እንስሳት እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርት አቅርቦትና ዋጋው ተመጣጣኝ መሆኑን ሸማቾች ተናገሩ።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ሸማቾች እንደገለፁት፤ የአትክልት ገበያው ከዚህ ቀደም ከነበረው እጅግ በጣም የቀነሰና የሸማቹን አቅም ያገናዘበ ነው።
በከተማዋ የበዓል ዋዜማ የእንስሳት ገበያውም የተሻለ አቅርቦት እንዳለውና ሁሉም እንደየአቅሙና ፍላጎቱ ለመገበያየት አመቺ መሆኑን ጠቁመዋል።
የከተማዋ ነዋሪ አቶ ዳኜ ገብሬ በበዓል ገበያው የእርድ ከብቶች አቅርቦት ፍላጎትን ያማከለ መሆኑን ገልፀው ሁሉም እንደየአቅሙና ፍላጎቱ ለመገበያየት አመቺ ነው ብለዋል።

አቶ በረከት ገብረማሪያም የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው በዘንድሮ ገበያ በሰንጋ በሬ እና የበግ ሙክት አቅርቦቱ የሚያረካና የሸማቹን አቅምና ፍላጎት ያማከለ መሆኑን ገልጸዋል።
በገበያው በቂ የዶሮ አቅርቦት እንዳለ የጠቆሙት ደግሞ ታዬ አጥናፉ የዕንቁላል ዋጋም ከዚህ ቀደም ከነበረው በቅናሽ እየተሸጠ መሆኑን አመልክተዋል።

በዘንድሮ የበዓል ገበያ ቀይ ሽንኩርት እና ነጭ ሽንኩርት አቅርቦት የተትረፈረፈ በመሆኑ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን አስረድተዋል።
በአጠቃላይ በጂንካ ከተማ የበዓል ገበያው የኢዜአ ሪፖርተር ባደረገው ቅኝት የተረጋጋና አቅርቦቱም የሚያረካ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል ።
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀዝሚ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ምርቶች ከአርሶ አደሮች ሸማቾች ጋር እስኪደርሱ በደላሎች አማካኝነት የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንደሚደረግባቸው ገልፀዋል።
እነዚህን ህገወጥ አሰራሮች ለመቅረፍ ፅህፈት ቤቱ ምርቶችን በማህበራትና በኢንተርፕራይዞች አማካኝነት ከአርሶ አደሩ ወደ ሸማቹ በቀጥታ እንዲቀርቡ በሰራው ስራ ያለ አግባብ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪን መከላከል መቻሉን ጠቁመዋል ።

በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይም በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚደረግ ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል በተቋቋመው የቁጥጥርና የክትትል ግብረ ኃይል አማካኝነት ህገወጥነትን የመከላከል ስራ ሲሰራ መቆየቱንም አንስተዋል።
በሌላ በኩል በበዓል ገበያው የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው፥ በበዓል ገበያውም በዕርድ እንስሳት እና በእንስሳት ተዋጽኦ እንዲሁም በቅመማ ቅመም እና በጤፍ ምርት ላይ የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩን አብራርተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026