🔇Unmute
ጎንደር ፤ጥር 3/2018(ኢዜአ)፡- በስራ ፈጠራ የሚሰማሩ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና "ኦርቢት ኢኖቬሽን ሀብ" የተባለ ድርጅት በጋራ በመሆን በስራ ፈጠራ ክህሎት ላሰለጠኗቸው 45 ወጣቶች ዛሬ የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ለሰልጣኞቹ እንደገለጹት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ልዩ የስራ ፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል።

የከተማ አስተዳደሩ ልዩ የስራ ፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ተቋማዊ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት ውጤታማና እንዲሆኑ ሁለተናዊ ድጋፍ በማድረግ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
የዲጂታል ቴክኖሎጂ በሀገራችን ለተዘመገቡ ኢኮኖሚያዊ እድገቶች አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ጠቁመው የሰራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በከተማው በማደራጀት ተሰጥዋቸውን ለሀገር ልማትና እድገት የሚያውሉበት ምቹ አውድ እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡
የጎንደር ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ተስፋሁን መኮንን እንደገለጹት የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች የዲጂታል ክህሎትና እውቀታቸው እንዲዳብር ኮሌጁ ተገቢውን የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡
የስራ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪነትን፣ ብቃትንና ዘመኑን የዋጀ መሆን እንዳለበት ጠቁመው ለስልጠናው የተመረጡ ወጣቶችም መስፈርቱን ያሟሉ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡

"የኦርቢት ኢኖቬሽን ሀብ" የኮሚኒቲ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም ማኔጀር ቅኔል ሃይሉ በበኩላቸው በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ራእይ ለማሳካት የዲጂታል ክህሎት ስልጠና የሚያገኙበት አሰራርን በመዘርጋት አየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎቸ በ6 ዙር የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በማወዳደር የቴክኖሎጂ ስልጠና እንዲያገኙ እየደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በጎንደር ከተማም 218 የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በማወዳደር ከዚህ ውስጥ መመዘኛውን ያለፉ 45 ወጣቶች ለሶስት ተከታታይ ወራት የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡
ከሰልጣኞቹ መካከል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር አዲሱ ወርቄ ስልጠናው በዲጂታል አለም ውስጥ የስራ ፈጠራ ሃሳቦቻችንን አንዴት ማሳካት እንደምንችል እውቀትና ክህሎት መጨበጥ እንድንችል አግዞናል ብለዋል፡፡
የሳይካትሪስት ባለሙያ የሆነችው ቤተልሄም ጌታቸው በበኩሏ የስራ ፈጠራ ሃሳቦቼን እንዴት ወደ መሬት ማውረድና ገበያ ላይ ማውጣት አንደምችል ስልጠናው የተሟላ እውቀትና ግንዛቤ ፈጥሮልኛል ብላለች።
በስነ ስርአቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችን ጨምሮ ስልጠናውን የተከታተሉ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡
ዱራሜ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርና ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችን ለልማት በማዋል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥ...
Jun 6, 2026
ደሎ መና፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የአርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያግዙ ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ...
May 26, 2026
ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክ...
May 21, 2026
አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...
Apr 29, 2026