🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የተቋማት ግንባታ እና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል የተሰናዳው የዐበይት ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፈዋል።
በዚህም ኮንፈረንሱ የኢኮኖሚ ሪፎርም ጉዞን መለስ ብሎ ለመገምገም እና የመጪውን ጊዜ የቅድሚያ ምልከታ ለማስቀመጥ የረዳ ጠቃሚ መድረክ እንደነበር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

የተቋማት ግንባታ እና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ በዚህ የተነሳ ነው የሀገራችንን የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ እርምጃዎችን የወሰድነው ብለዋል።።
በፊስካል አስተዳደር፣ በሞኒተሪ እና ፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም በገቢ አስተዳደር፣ በካፒታል ገበያ አስተዳደር፣ በኢንቨስትመንት አስተዳደር እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ሪፎርም ያሳካናቸውን ድሎች ለማጤን ያገዘ እና የሪፎርሞቹን ጉዞ ፍጥነት አጥብቆ በመያዝ የመራመድን እና ሰፊውን የኢኮኖሚ ሽግግር አጀንዳ የማላቅን አስፈላጊነት ለመገንዘብ የረዳ መድረክ ነበር ሲሉም ነው የገለጹት።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026