የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ ፍትሃዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል 

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በከተሞችም ይሁን በገጠር የልማት ተደራሽነትን በማስፋት ፍትሃዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን መሀመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን መሀመድ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የልማት ተደራሽነትን በማስፋት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥና የጋራ ብልጽግናን እውን የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከከተሞች በተጨማሪ ለገጠር አካባቢዎችም ተመሳሳይ ትኩረት በማድረግ የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ ለመቀየር የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህ የልማት እቅድ መሳካትም ከመንግስት ጥረት በተጨማሪ ባለሃብቶች፣ አጋር ተቋማትና አጠቃላይ የህብረተሰቡ ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።


የክልሉ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ቢሮ ሃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር)፤ የገጠር ልማትን ለማሳካትና የመንገድ ተደራሽነትን ለማስፋት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ዘመናዊና ስማርት ከተሞችን እውን የማድረግ እና የገጠር ቀበሌዎችን በመንገድ በማስተሳሰርና የገጠር ኮሪደር ልማትን ለማሳካት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑም አንስተዋል።

በዚህም በክልሉ እስካሁን ከ2 ሺህ 664 በላይ የገጠር ቀበሌዎችን በመንገድ ማስተሳሰር መቻሉን ተናግረዋል።

በቀጣይም በገጠር ከመንገድ መሰረተ ልማት ባሻገር ሌሎች ተያያዥ መሰረተ ልማቶች የሚከናወኑ መሆኑን አንስተው የኮሪደር ልማቱ በተመረጡ አካባቢዎች በመጀመር የሚሰፋ ይሆናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026