የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የገጠር መሬትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ የካቲት 18/2018(ኢዜአ)፦ የገጠር መሬትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር አርሶአደሩየኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሬትና ህብረት ስራ ማደራጃ ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "ብሔራዊ መታወቂያ ለገጠር መሬት ባለይዞታዎች" በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ አካሂዷል።


በግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ትዕግስቱ ገብረመስቀል እንደገለፁት፤ የገጠር መሬትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር የአርሶ አደሩን ዘላቂ የመሬት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና ብልሹ አሰራርን ማስቀረት ይቻላል።

አርሶ አደሩ ማሳውን አስይዞ የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ እንዲችልም የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ካሉት ከ50 ሚሊዮን በላይ የአርሶ አደር ማሳዎች መካከል 32 ሚሊዮን ለሚሆኑት የባለቤትነት ይዞታ መሰራቱን ለአብነት አንስተዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፤ የገጠር መሬትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማስተሳሰሩ ሂደት አርሶ አደሩን በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።


ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመተግበር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሆነም አስረድተዋል።

ትግበራው የመሬት አስተዳደርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲካሔድ በማድረግ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል ሲሆን መሬትን ለተፈለገው አገልግሎት ለመጠቀም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።

የክልሉ መሬትና ህብረት ሥራ ማደራጃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ካሚል ሀሚድ በበኩላቸው፤ ‎በክልሉ ለ277 ሺህ 274 ማሳዎች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሠጠቱን ነው የተናገሩት።


‎አርሶ አደሩ የመሬት ባለቤትነት መብቱን በመጠቀም ማሳውን በማልማት፣ በማከራየት እንዲሁም ከባንክ ጋር በማስተሳሰር የብድር አቅርቦት ማግኘት እንደሚችል ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ የፌዴራል፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026