የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

4ኛው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም መጋቢት 17 እና 18 ቀን 2018 በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦ 4ኛው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ የኢንቨስትመንት ፎረም መጋቢት 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ፎረሙን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ፎረሙ በኮሚሽኑ፣ በገንዘብ ሚኒስቴርና በአጋር የልማት ድርጅቶች ትብብር የተዘጋጀ ነው።

የመድረኩ ዋና ዓላማ አዳዲስ የውጭና የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ፣ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ማሳየት እንዲሁም በቅርቡ የተደረጉ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለባለሀብቶች ማስተዋወቅ ነው ብለዋል።

በፎረሙ ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ ኩባንያዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አማካሪዎችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት ዕድሎች በማስተዋወቅና የፎረሙን ስኬት በማብሰር በኩል የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በበኩላቸው፤ መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት ሰፊ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረጉን ገልጸዋል።

በሀገሪቱ ባሉ እምቅ አቅሞችና በመንግስት የሪፎርም ስራዎች ምክንያት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ መነሳሳት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ይህ ፎረም በእነዚህ ዕድሎች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ትልቅ መድረክ እንደሚሆንም አስረድተዋል።

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ የደቡብ ሱዳንና ሱዳን ዳይሬክተር ሜርየም ሳሊም እንዳሉትም፤ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ አቅም በመጥቀስ በፎረሙ ለመሳተፍ አሁን ትክክለኛው ጊዜ ነው ብለዋል።

ወጣትና እያደገ ያለ የሰው ኃይል መኖሩ፣ ስትራቴጂካዊ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ፣ ጠንካራ የግብርና መሠረትና እየሰፋ ያለ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዳይሬክተሯ ለኢትዮጵያ ተመራጭነት እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በተስፋ ብቻ ሳትወሰን በተግባር የሚታዩ የሪፎርም እርምጃዎችን እየወሰደች በመሆኗ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026