🔇Unmute
ጋምቤላ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በግብርና በማዕድንና በሌሎች የልማት ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።
የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው መደበኛ ጉባኤ የክልሉን የግማሽ በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል።
ርዕሰ መስተዳድሯ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ በሰላም ግንባታ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በገቢና በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በሕዝቡና በፀጥታ አካሉ የተደረገው የተቀናጀት ጥረት የተረጋጋ ሰላም ማምጣት አስችሏል ነው ያሉት።
በ2017/18 የምርት ዘመን ከ186 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉንም ገልፀዋል።
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ እንዳለው በሪፖርቱ አመላክተዋል።
በማዕድን ልማት ዘርፉም በመጀመሪዎቹ ስድስት ወራት 3 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ 3 ሺህ 860 ኪሎ ግራም መግባቱን ጠቅሰዋል።
አፈፃፀሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1 ሺህ 057 ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለው ነው የገለጹት።
የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራትም በግማሽ ዓመቱ ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን በሪፖርቱ አመላክቷል።
በተጨማሪም በትምህርት፣ በጤና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በስራ ዕድል ፈጠራና በሌሎች የልማት መስኮች አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026