🔇Unmute
ጎንደር፤መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የነዳጅ አቅርቦት ችግርን ለመፍታትና የተቀመጠውን ስትራቴጂ ለማሳካት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ ስራ መግባቱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው ነዳጅን በቁጠባና በፍትሃዊነት ለመጠቀም እንዲቻል በተቀመጠው ስትራቴጂ ዙሪያ በጎንደር ከተማ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ውይይት አካሄዷል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ዋና አማካሪ መሃመድ ጀማል (ዶ/ር) እንደገለፁት አለም አቀፍ የነዳጅ ቀውሱ እያሳደረ ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመሻገር በክልሉ በየደረጃው የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ነዳጅን ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል በቁጠባና በፍትሃዊነት በመጠቀም ረገድ ቅድሚያ ለተሰጣቸው የትራንሰፖርት ዘርፎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል፡፡
ፍትሃዊ የነዳጅ ስርጭት ስርዓትን በማስፈን ህገ ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጠጣርና እርምጃም ለመውሰድ እንዲቻል ግብረ ሃይሉ በየደረጃው ተልኮ ተቀብሎ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘና ግምቱ ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 300 ሺህ ሊትር ናፍጣና 155 ሺህ ሊትር ቤንዚን በውርስ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ችግሩን ለመሻገር መንግስት ያስቀመጣቸውን የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአግባቡ በመተግበር ረገድ ህብረተሰቡ ሰፊ ትብብርና ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
ህዝቡ አጫጭር መንገዶችን በእግሩ በመጓዝ እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርቶችን በአማራጭነት መጠቀም ችግሩን ለመሻገር ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበትም አመልክተዋል፡፡

የጎንደር ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ አለልኝ አይለው በበኩላቸው የነዳጅ አቅርቦት ችግሩን ለመቋቋም በከተማ አሰተዳደሩ የተቋቋመው ግብረ ሃይል ህገ ወጥ የነዳጅ ዝውውርና ግብይትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው፡፡
አለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ሲስተጓጎል በሀገራችን ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ በጋራ መሻገር ይገባል ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ናቸው፡፡
የከተማው የፀጥታና የፍትህ አካላት በህገ ወጥ የነዳጅ ንግድና ዝውውር ላይ የተሰማሩ ማደያዎችንና ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ለህግ በማቅረብና አፋጣኝ የህግ እርምጃ በመውሰድ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በነዳጅ ስርጭትና በትራንሰፖርት ዘርፉ ላይ የተሰማሩ አካላትን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026