🔇Unmute
አክሱም ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በአክሱም ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የተሰማሩ ወጣቶች ለፋሲካ በዓል የዶሮና እንቁላል ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ገለጹ።
በአክሱም ከተማ በርካታ ወጣቶች በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በመሳተፍ ስኬታማ እየሆኑ ይገኛሉ።
በተለይም በዶሮ አርባታ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ለበዓል ገበያ እንቁላልና ዶሮዎችን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው።
በዚሁም መሰረት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ዶሮዎችን ለፋሲካ የበዓል ገበያ ለማቅረብ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው ወጣቶች ገልጸዋል።
በዘርፉ ልማት ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል በረከት ግደይ፤ ለፋሲካ በርከት ያሉ ዶሮዎችና እንቁላል በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግሯል።

ከብድርና ቁጠባ ተቋም በተገኘ ብድር እና ከቤተሰብ ድጋፍ ተደርጎለት እርባታውን መጀመሩን የሚገልጸው በረከት በአጭር ጊዜ ስኬታማ መሆኑን ይናገራል።
በ2 ሺህ 500 ጫጩቶች ስራ መጀመሩን አስታውሶ አሁን ላይ በየእለቱ እንቁላል ለገበያ በማቅረብ ገቢ እያገኘ መሆኑን ገልፆ ለፋሲካ በአል ደግሞ የእርድ ዶሮዎችን ጨምሮ እንቁላል በልዩ ሁኔታ ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ተናግሯል።
ሌላኛው ወጣት ገብረመድህን ተኽሉ፤ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተሰማርቶ በዶሮ እርባታ ስራ እራሱንና ቤተሰቡን እያገዘ መሆኑን ገልጿል።

ለፋሲካ በዓል በርከት ያሉ ዶሮዎችንና እንቁላል በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን አንስቶ በዚህም እራሱን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለማህበረሰቡ ጥሩ አቅርቦት የሚሰጥ መሆኑን ነው የገለጸው።
በአክሱም ከተማ የግብርና ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሉ ገብረህይወት፣ በከተማዋ በሌማት ትሩፋት የተሰማሩ በርካታ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የወጣቶቹ የልማት ጥረት ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠርና የአካባቢው ማህበረሰብ በምርቶች ተጠቃሚ እንዲሆን እያስቻሉ ይገኛሉ ብለዋል።
በዚህም መሰረት በከተማዋ በሌማት ትሩፋት የተሰማሩ ወጣቶች በተለይም የዶሮ እና እንቁላል እንዲሁም ሌሎች ተዋጽኦዎችን ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026