የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ለትንሳኤ በዓል የግብርና ምርቶች የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል

Apr 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በሐረር ከተማ ለትንሳኤ በዓል የሚያስፈልጉ የግብርና ምርቶች የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ገለጸ።

ለበዓሉ የሚያስፈልጉ የግብርና ምርት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መኖሩንም ሻጭና ሸማቾች ተናግረዋል።

የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ምርቶች እጥረት እንዳይከሰት ከሁሉም የንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተደርጓል።

የምርት አቅርቦትን ከማሳለጥ አንጻርም ከክልሉ ገጠር ወረዳዎች የሚመረተውን ምርት ወደ ከተማው የማቅረብና ከተለያዩ አቅራቢዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ምርት ወደ ከተማው እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል።

እንዲሁም የምስራቅ እዝ ያመረተውን ምርት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲዳረስ ለሸማቾች ማህበራት እያቀረበ መሆኑንም አመልክተዋል።

በተጨማሪም በከተማው የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ ስፍራዎችን የማጠናከር ስራ መስራቱን ጠቁመዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን ያልተገባ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎችን የመከታተልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት እየተፈጸመ መሆኑን አመልክተዋል።

በከተማው በተለምዶ ሞቢል በተባለው የቅዳሜና እሁድ ገበያ በአትክልት ሽያጭ የተሰማሩት ወይዘሮ በቀለች ንጉሴ ከአካባቢውና ከሌሎች ስፍራ አትክልት ለተጠቃሚው እያቀረቡ መሆኑን ጠቅሰዋል።


ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ ህዝቡ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፍ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የበዓል ገበያ የምርት አቅርቦቱ የተሻለ መሆኑንና የክልሉ ንግድ ጽህፈት ቤት ባወጣው ዋጋ መሰረት ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጡ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የግብርና ምርት ነጋዴ የሆኑት ኢሳያስ አለማየሁ ናቸው።


ለትንሳኤ በዓል አትክልት፣ እንቁላልና ሌሎችም ምርቶች አቅርቦት መኖሩን የተናገሩት ደግሞ በስፍራው አትክልት በመሸመት ላይ የነበሩት ወይዘሮ ሃይማኖት የሺጥላ ናቸው።


ለበዓሉም የሚያስፈልገውን በአቅማቸው እየሸመቱ እንደሚገኙ የጠቀሱት ወይዘሮ ሃይማኖት ያልተገባ ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር መጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026