የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የበጋ ስንዴ ልማት አርሶ አደሩ ከራሱ ፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚሆን ምርት ለማቅረብ አስችሏል

Apr 15, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር ፤ሚያዚያ 6/2018 (ኢዜአ)፡-በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተካሔደው የበጋ ስንዴ ልማት ስራ አርሶ አደሩ ከራሱ ፍጆታ አልፎ ለገበያ የሚሆን ምርት ለማቅረብ ማስቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ ዘንድሮው በተካሄደው የበጋ ወቅት የመስኖ ስንዴ ልማት ስራ ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ለገበያ ማቅረብ መቻሉም ተገልጿል፡፡

በመምሪያው የመስኖ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሀውልቱ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ኢንሼቲቭ አርሶ አደሩ ዓመቱን ሙሉ የሚያመርትበትን አዲስ የስራ ባህል ፈጥሯል።

በዞኑ ከአራት ዓመት በፊት በበጋ መስኖ ስንዴ የሚለማው መሬት ከአራት ሺህ ሄክታር የማይበልጥ፤የሚገኘው ምርት ደግሞ ከ112 ሺህ ኩንታል የዘለለ እንዳልነበረ አስታውሰዋል።

በዘንድሮ የበጋ ወቅት ደግሞ ከ29 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ዓመታዊ ምርቱን ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ለማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

የበጋ ስንዴ ልማት ስራ አርሶ አደሩ ከራሱ ፍጆታ ባለፈ ለአግሮ ኢንዱሰትሪዎች ግብአትና ለገበያ የሚሆን ምርት በማምረት ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ማስቻሉን ነው የገለጹት፡፡

በዚሁ ወቅት አርሶ አደሩ ምርታማነትን እንዲያሳድግም አዳዲስና ዘመናዊ የግብርና አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ተግባራዊ እንዲያደርግም የባለሙያዎች እገዛ ከፍተኛ አስተዋጽአ ማበርከቱን ነው የተናገሩት።

የኩታ ገጠም እርሻ፤ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ተሞክሮችን በመጠቀም በዘላቂነት ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲቻል በትኩረት መሰራቱን አስረድተዋል።

በዞኑ የወገራ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር መላኩ ቸርነት ፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራ ለራስ ፍጆታ ብቻ የነበረውን አመራረት በመቀየር ለገበያ የሚተርፍ ምርት ማግኝት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

በዘንድሮ በጋም በአንድ ሄክታር መሬት ካለሙት የስንዴ ሰብል 36 ኩንታል ስንዴ በማምረት ለገበያ አቅርበው ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የሚገልጹት፡፡

በምእራብ ደንቢያ ወረዳ የዋዋ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር የሻምበል መንግስቱ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው በጋ በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ ካለሙት የሰንዴ ሰብል 18 ኩንታል ምርት አግኝተዋል።

ያገኙት ምርትም ከራሳቸው አልፎ ለገበያ ለማቅረብ መቻላቸውን ነው ያስታወቁት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል-ሰልጣኞች

አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...

Apr 29, 2026

በአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድ የሚወሰድበት ነው

ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...

Apr 15, 2026

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው

ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...

Apr 14, 2026

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025