የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በአማራ ክልል ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞችን የመትከል ሥራ ተጀመሯል

Apr 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞችን የመትከል ሥራ መጀመሩን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ አስታወቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ የተቀናጀ የፍራፍሬ ክላስተር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።


ይህ መርሃ ግብር የተጀመረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የተገነባውን የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት በመረቁበት ወቅት አካባቢው ካለው አመቺ ተፈጥሯዊ ሁኔታ አኳያ የተቀናጀ የግብርና ልማት ሊተገበርበት እንደሚገባ የገለጹትን መነሻ በማድረግ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በወቅቱ የሎጎ ሐይቅን ውበትና ልማት ይበልጥ ትርጉም ባለው መልኩ ለማስቀጠል የተፈጥሮ ሀብትን ከምርታማነት ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባም መናገራቸው ይታወሳል።

የአካባቢው ስነ-ምህዳር ምቹ በመሆኑ በስፋት የፍራፍሬ ልማት ሊከናወን እንደሚገባ አመልክተው፤ ከፍራፍሬ ተከላው ጎን ለጎን የከብትና የዶሮ እርባታን በማስፋፋት የአካባቢውን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚቻል መናገራቸው ይታወሳል።

ሎጎ ሐይቅን ውብ፣ አረንጓዴና ለነዋሪውም ሆነ ለጎብኚው ምቹ በማድረግ አከባቢውን "የጥጋብ መንደር" መሆን እንደሚችል በወቅቱ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ሲጀመር እንደተናገሩት፤ በክልሉ አግሮ-ኢኮሎጂን መሰረት ያደረገ የቡናና የፍራፍሬ ልማት በዚህ በጋ በስፋት ተጀምሯል።

ስራው በ14 ዞኖች፣ በ33 ወረዳዎች እና በ40 ቀበሌዎች መጀመሩን ተናግረው፤ በአጠቃላይ ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ገልጸዋል።

በሁሉም አካባቢዎች 4 ሺህ 225 ሄክታር መሬት ለማልማት ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል።

ሎጎ ኃይቅ አካባቢ አርሶ አደሮች በሙሉ ፍላጎታቸው ጫትን በምርታማ የፍራፍሬ ተክሎች ለመተካት ትልቅ ተነሳሽነት እያሳዩ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን በበኩላቸው፤ በዞኑ ያለውን የተበጣጠሰ የአመራረት ዘዴ በመቀየር በክላስተር የማልማት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ በጋ ወቅት ብቻ በ5 ወረዳዎች 830 ሄክታር መሬት በክላስተር ለመትከል መለየቱን ተናግረው፤ በዋናነት ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓዬ እና አቮካዶ ላይ ትኩረት መደረጉን ጠቅሰዋል።

ቃሉ፣ አርጉባ፣ ተሁለደሬ፣ አምባሰል እና ወረባቦ ወረዳዎች ለዚህ ስራ የተለዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ይህ ስራ አርሶ አደሩን ከጫት ጥገኝነት በማውጣት በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የፍራፍሬ ምርቶችን በስፋት እንዲያመርትና ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደሮችም በልማቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አርሶ አደር አለባቸው ሰይድ ከዚህ ቀደም ማሳቸው በጫት የተሸፈነ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ግን ካለው የተሻለ ገቢና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አኳያ ሙዝ እና የተለያዩ ፍራፍሬ ችግኞች መትከላቸውን አብራርተዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አልጋነሽ ንጋቱ፤ ማሳቸውን ወደ ሙዝ ልማት መቀየራቸው ገቢያቸውን ከማሳደግ ባለፈ ልጆቻቸውን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።

በአካባቢው የተገነባው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት በአርሶ አደሩ ዘንድ አዲስ መነሳሳትን መፍጠሩን ጠቅሰው፤ የተጀመረውን የልማት ንቅናቄ ግብ ለማድረስ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ያረጋገጡት አርሶ አደር ፋንታው አህመድ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026