🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያጋጠሟትን ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
“የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የኮሮና ወረርሽኝ ያስከተለው ዓለም አቀፍ ቀውስ እና የአጎዋ ስምምነት መቋረጥ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ነፃነት አዲስ የማንቂያ ደወል መሆናቸውን ገልጸዋል።
እነዚህን ተግዳሮቶች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማነቃቃት አራት ስልታዊ ምሰሶዎች ያሉት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ መደረጉን አስረድተዋል።
ከነዚህ ስልቶች መካከልም ዋነኛው የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራ ሲሆን፣ ይህም በዘርፉ ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠሩን አመልክተዋል።
በዚህ የለውጥ እርምጃ ማግስት 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ ፊቱን ወደ አምራችነት እንዲያዞር ካደረገው ተነሳሽነት ጋር ተያይዞ፣ በአሁኑ ወቅት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የፈቃድ ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻሉን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
ይህ ዕድገት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በ22 ነጥብ 7 በመቶ እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ፣ ለዘርፉ የሚቀርበው የኃይል መጠን እንዲያድግ ምክንያት መሆኑን ነው ያብራሩት።
ሌላኛው ትኩረት ያረፈው የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ላይ ሲሆን፣ ቀደም ሲል 90 በመቶ የነበረውን የውጭ ጥገኝነት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን አስረድተዋል።
በአሁኑ ወቅት እንደ ቢራ ገብስ፣ ጨርቃጨርቅና ስንዴ ያሉ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉና በከፊል ማምረት መጀመሩን ጠቁመዋል።
ለዚህ ስኬት በአራት የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ዙሪያ የተደራጁ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ለፋብሪካዎች ግብዓት በማቅረብ ረገድ የጀርባ አጥንት መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝርዝር አብራርተዋል።
በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የነበሩ ነገር ግን በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች፣ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውን ጠቁመዋል።
ይህም የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ እንዲል በማድረግ፣ በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ትልቅ እመርታ መፍጠሩን ገልጸዋል።
የመጨረሻው ስልታዊ ምሰሶ የሆነው ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት፣ ቀደም ሲል ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ማስቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው አረጋግጠዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026