🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦በሸገር ከተማ ካለው የመልማት አቅም ጋር የሚመጣጠን ኢንቨስትመንትን መሳብ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ ገለጹ።
በከተማዋ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት የሚዲያ አካላትን ያሳተፈ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄዷል።
በዚሁ መርሐ ግብር በገላንና በየካ ጣፎ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ተጎብኝተዋል።
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፤ ከተማዋ ያላትን የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አቅም ተጠቅማ የኢኮኖሚ ማዕከል እንድትሆን እየተሰራ ይገኛል።
ይህም የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገት ከመደገፍ ባለፈ የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተማዋ ከአዲስ አበባ ጋር ያላት ቅርበት ለሎጂስቲክስ ማዕከልነት ምቹ እንደሚያደርጋት ጠቅሰው፥ ያለው ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት ለንግድና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ትልቅ ዕድል መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የኢንቨስትመንት ሥራዎችም ካለው አቅም ጋር የሚመጣጠን እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተማዋ ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት በኢንቨስትመንት ዘርፉ ውጤታማነት እየታየና በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች መካከል የዊንፊልድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ናደው ጥላሁን፤ የሸገር ከተማ አስተዳደር ባመቻቸው የኢንቨስትመንት ዕድል በተሽከርካሪ ንግድ ዘርፍ መሰማራታቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውንና ወደፊትም ፕሮጀክቱን ለማስፋት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የብራይተን ትሬዲንግ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዳታ ጁነዲን በበኩላቸው፤ ትልቅ የማምረቻ ፋብሪካ አቋቁመው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
እነዚህ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጥገናና ሽያጭ ላይ የሚሰሩ ሲሆን፤ይህም የአቅርቦት እጥረትን ከመቅረፍ ባለፈ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለከተማዋና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተገልጿል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026