የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በኦሮሚያ ክልል ቆላማ አካባቢዎች ድርቅን በዘላቂነት መቋቋም የሚያስችል የመኖ ልማት በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ነው

Apr 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ሚያዝያ 13/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ቆላማ አካባቢዎች ድርቅን በዘላቂነት መቋቋም የሚያስችል የመኖ ልማት በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ መስኖና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ድርቅን በዘላቂነት መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጿል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሮባ ቱርጬ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በአርብቶ አደር እና ቆላማ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት በእንስሳት ሀብቱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የሚቀንሱ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ሰፊ መሬት በእንስሳት መኖ የማልማት ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።


መኖ የሚለማባቸው አካባቢዎች ከእንስሳት ንክኪ ነፃ ሆነው እንዲጠበቁ በማድረግ አርብቶ አደሩ በባለቤትነት እንዲንከባከባቸው እየተደረገ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

ሌላው ድርቅን በዘላቂነት ለመቋቋም እየተከናወነ ያለው ተግባር አርብቶ አደሩን ወደ ከፊል አርሶ አደርነት ለመቀየር እየተደረገ ያለው ጥረት አካል መሆኑንም ገልጸዋል።

ለዚህም በክልሉ ቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች አነስተኛ እና መለስተኛ የመስኖ ግድቦችን በመገንባት የቆላ ግብርናን የማልመድ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት ለሰውና ለእንስሳት መጠጥ ውሃ ቅድሚያ በመስጠት ግንባታቸው ከተጀመሩ 71 አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ግድቦች መካከል 37ቱ በቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው ብለዋል።


ከእነዚህ 37 ፕሮጀክቶች መካከል 34ቱ ተጠናቅቀው በአሁኑ ወቅት ለሰውና ለእንስሳት መጠጥ፣ ለዓሣ እርባታ እንዲሁም ለመስኖ ልማት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም አስረድተዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በታየው ውጤት ድርቅን በራስ አቅም መቋቋም በመቻሉ፣ ከሌላ አካባቢ ምንም አይነት መኖ አለመጫነኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

በክልሉ አርብቶ አደር አካባቢዎች 17 ትላልቅ የመኖ ማከማቻ ማዕከላት እየተገነቡ ሲሆን፣ የመኖ ልማቱን የሚጎዱ መጤ አረሞችን በመከላከል እንዲሁም አካባቢውን በመጠበቅ ልማቱ እንዲጠናከርም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026