🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የቻይና ባለሃብቶችን የንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እያሳደገ መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ።
አምባሳደር ቼን ሃይ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና ታሪካዊና ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።
የኢትዮ-ቻይና ታሪካዊ ግንኙነት የልማት ትብብርን በማጎልበት የሀገራቱን ሁለንተናዊ ግንኙነት እያጠናከረ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የሀገራቱ የሁለትዮሽ የንግድና ኢንቨስትመንት ስትራቴጂክ አጋርነት ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገብ የጋራ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።
የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚሰማሩባቸው አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎችም ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገቡ መሆኑን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያም የቻይና አልሚ ባለሃብቶችን የኢንቨስትመንት በራስ መተማመን በማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል።
ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የፈጠረው የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢም አዳዲስ ዕድሎችን መጠቀም የሚሹ በርካታ የቻይና ባለሀብቶችን እየሳበ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የኢትዮ-ቻይና የኢኮኖሚ ትብብርም በግብርና፣ ኢንዱስትሪና የሰው ሃብት ልማት ሶስት ወሳኝ ምሰሶዎችን ማዕከል በማድረግ በስፋት እየተሰራበት መሆኑን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ፈጣን የልማትና የዕድገት አቅጣጫ የሀገራቱን ስትራቴጂክ አጋርነት በማጠናከር ከፍተኛ አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል።
የቻይና ባለሃብቶች የኢትዮጵያ የንግድና የአምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ተሳትፎም የኢኮኖሚ ልማትና ሽግግርን በማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የሀገራቱ በሰው ሃብት ልማት ትብብር የአዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በክህሎት የበለፀጉ ዜጎችን በማፍራት ወሳኝ ሚና እየተወጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በሚቀጥሉት ዓመታትም የሀገራቱን የንግድና ኢንቨስትመንት ስትራቴጂክ አጋርነት የበለጠ በማጠናከር የሁለትዮሽ ግንኙነትን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026