🔇Unmute
ጅማ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ለህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የብልጽግና ጉዞን የማፋጠን ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ ገለጹ።
በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ በመንግስት እና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጀምረው ሳይጠናቀቁ የመቅረት ችግር ነበር።
ባለፉት አምስት እና ስድስት ዓመታት ግን በርካታ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።
ፕሮጀክቶች ለረጅም ዓመታት ሳይጠናቀቁ መቆየታቸው ህዝቡን ተስፋ ከማሳጣቱ ባለፈ ለከፍተኛ የሀብት ብክነት ምክንያት ሆኖ መቆየቱንም ጠቅሰዋል።
በአሁኑ ወቅት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በብዛት ተገንብተው ለአገልግሎት የሚበቁበት አዲስ የሥራ ባህል መፈጠሩንና ይህም የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
"አሁን ላይ ፕሮጀክቶች በጥራት እና በብዛት እየተገነቡ የህዝቡም የልማት ጥያቄ እየተመለሰ ይገኛል'' ሲሉም ገልጸዋል።

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የነዋሪዎችን የልማት እና የሰላም ጥያቄ ለመመለስ የተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ማህበረሰቡ ምቹ እና የተሟላ አገልግሎት ማግኘት እንደሚፈልግ የጠቀሱት አስተዳዳሪው፤ ይህንን ፍላጎት ለማርካት የሚያግዙ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ህንፃዎች ተገንብተው መመረቃቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይም ቀሪ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በዛሬው እለትም የኦሞ ናዳ ወረዳ አስተዳደር እና የከተማ አስተዳደር ህንፃዎች የተመረቁ ሲሆን፣ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ወጪ መደረጉን ገልጸዋል።
የተመረቁ ፕሮጀክቶችም ለወረዳው ነዋሪዎች የተቀላጠፈና ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026