የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል

Jul 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ዲላ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ እንደሚጠናከር የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ የ2018/19 የመኸር አዝመራ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በዲላ ከተማ ተካሂዷል።


በመድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በክልሉ በተያዘው የመኸር እርሻ በቋሚና በዓመታዊ ሰብሎች ከ909 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይለማል።

በክልሉ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ በተያዘው የመኸር ወቅትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የመኸር ወቅት ከ855 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ከታቀደው በላይ ምርት ለመሰብሰብ መቻሉን አስታውሰው፣ በ2018/2019 የመኸር ወቅትም በቋሚና ዓመታዊ ሰብሎች ከ909 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይለማል ብለዋል።

ከዚህም ከ77 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደተግባራዊ ሥራ መገባቱን ነው የገለጹት።

በክልሉ በ2018/19 የመኸር እርሻ ፈጥነው የሚደርሱ ጤፍ፣ ቦሎቄና መሠል ሰብሎች እንደሚለሙ የተናገሩት ኃላፊው፣ በቆሎ ማሽላ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ቡና፣ እንሰትና የሥራስር ሰብሎችም እንደሚለሙ አመልክተዋል።


በዞኑ ዘመናዊ የግብርና አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደተቻለ ያነሱት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ናቸው።

ለዚህም በቋሚ ሰብሎች በተለይ በቡናና እንሰት ምርታማነት የመጣው ውጤት ተጠቃሽ መሆኑን አንስተው፣ ክፍት መሬቶችንም ጭምር በማልማት የመኸር እርሻን ዕቅድ ለማሳካት ይሰራል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የክልሉ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026