የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኦንላይን አገልግሎት መጀመሩ የሲቪልና የነዋሪነት አገልግሎትን ባለንበት ሆነን እንድናገኝ አስችሎናል 

Jul 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/ 2018 (ኢዜአ):- ኤጀንሲው ያስጀመረው የኦንላይን አገልግሎት የሲቪልና የነዋሪነት አገልግሎትን ባሉበት ሆነው በቀላሉ እንዲያገኙ ማስቻሉን ተገልጋዮች ገለጹ፡፡

አገልግሎቱ በተጀመረ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ3ሺህ 600 በላይ ነዋሪዎች የዲጂታል አገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከትውልድ እስከ ሞት ያሉ ወሳኝ ኩነቶችን የሚመዘግብ ተቋም ነው፡፡

ይህንን የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ሰፊ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ በቅርቡም አዲሱን ዲጂታል ስርዓት በስኬት አስመርቆ ስራ አስጀምሯል።

ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ወይም በኮምፒውተራቸው አማካኝነት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ምቹ አሰራር የፈጠረ ነው።

በኦንላይን የተጀመሩት አራቱ ዋና ዋና አገልግሎቶችም መታወቂያን ከፋይዳ መረጃ ጋር ማስተሳሰር፣ የነዋሪነት መታወቂያ እድሳትና የጠፋን መተካት፣ ያላገባ የምስክር ወረቀት አገልግሎት እና የልደት ምስክርነት ወረቀት አገልግሎት ናቸው።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ፤አዲሱ የዲጂታል አሰራር ጊዜን በመቆጠብ፣ ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ ትልቅ ጠቀሜታ እያገኙበት መሆኑን ነው ያረጋገጡት።

ከተጠቃሚዎች መካከል የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ነዋሪ አቶ አባትዬ ተስፋዬ ፤ አገልግሎቱን በቀላሉ ከቤታቸው ሆነው በቴክኖሎጂው አማካኝነት ማጠናቀቃቸውን ገልጸው፣ የተዘጋጀላቸውን መታወቂያ ለመረከብ ብቻ ወደ ወረዳው መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ይህ አሰራር ጊዜን ከመቆጠቡ ባለፈ፣ ዘመናዊና ስልጡን አሰራር በመሆኑ ከፍተኛ እርካታ እንደፈጠረላቸውም ጨምረው አስታውቀዋል።

ሌላኛው የዚሁ ወረዳ ነዋሪና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ኢሳያስ ግርማ በበኩላቸው፤ የዲጂታል አሰራሩ ጊዜን ከመቆጠብ ባለፈ በዘርፉ ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ አንጻር አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ወይም በኮምፒውተራቸው አስፈላጊውን ሰነድ አያይዘው ካመለከቱ በኋላ የሚፈልጉት አገልግሎት በፍጥነት እየተሰጣቸው ይገኛል ያሉት ደግሞ በኤጀንሲው የኦንላይን አገልግሎት ባለሙያ የሆኑት ደሳለኝ ዘርጋ ናቸው።


ተገልጋዩ ወደ ወረዳ በአካል የሚመጣው የተዘጋጀውን ሰርተፊኬት ወይም መታወቂያ ለመውሰድ ብቻ መሆኑን ባለሙያው አብራርተዋል።

ሌላኛዋ የኤጀንሲው የኦንላይን አገልግሎት ባለሙያ ሶስና አወል በበኩላቸው ፤ይህ አሰራር ቀደም ሲል በወረዳዎች ላይ ይፈጠር የነበረውን ከፍተኛ የህዝብ ግርግርና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰው ይገኛል ብለዋል።


ይህም ሰራተኞች በተረጋጋ መንፈስና በነጻነት ስራቸውን በጥራት እንዲያከናውኑ ትልቅ እገዛ ማድረጉን አክለዋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ በበኩላቸው፤ አዲሱ የኦንላይን አገልግሎት አሰጣጥ በተቋሙ ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት መቆራረጦችንና የተገልጋይ እንግልትን በከፍተኛ ደረጃ እየቀረፈ መሆኑን አስታውቀዋል።


አገልግሎቱ በተጀመረ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ3ሺህ 600 በላይ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሆነው በቴክኖሎጂው መጠቀም መቻላቸውን ለአብነት አንስተዋል።

የኦንላይን አገልግሎቱ በተገልጋይና በአገልግሎት ሰጪዎች መካከል ያለውን ቀጥተኛ ንክኪ በማስቀረት ብልሹ አሰራርን በጽኑ የሚከላከል መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂንና ስማርት ከተማ የመፍጠር ግብን የሚያሳካ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026