🔇Unmute
አዳማ ፤ ሰኔ 21/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀናጀ የሰብል ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው የ2018/19 የምርት ዘመን የሰብልና ፍራፍሬ ጥበቃና እንክብካቤ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ በወቅቱ፤ በክልሉ ግብርናውን ለማዘመንና ውጤታማ ለማድረግ የተነደፉት ኢኒሼቲቮች አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ችለዋል።
ለዚህ ስኬት ደግሞ የሰብል ጥበቃና እንክብካቤ፣ የግብዓት አቅርቦት፣ የአፈር ለምነት አጠባበቅ እንዲሁም የባለሙያ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ምክትል ኃላፊው አንስተዋል።
በተጨማሪም የሰብል ልማትን በሽፋንም ሆነ በምርታማነት ዘላቂ ለማድረግ ከግብርና ምርምር ማዕከላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አክለው ገልጸዋል።
የሰብል ምርትና ምርታማነትን የሚጎዱ አረም፣ ተባይና በሽታዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቆጣጠር ሳይንሳዊ መንገዶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የዛሬው የንቅናቄ መድረክም የዘርፉ አመራሮችና በየደረጃው የሚገኙ የሰብል እንክብካቤ ባለሙያዎች ይህንኑ ስኬት በጋራ ለማሳካት እንዲረባረቡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ከሰብል ጥበቃው በተጨማሪ፣ አሲዳማነታቸው የጨመረና ምርታማነታቸው የቀነሰ መሬቶችን በኖራና በተፈጥሮ ማዳበሪያ በማከም ረገድ ሰፊ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል።

የቢሮው የሰብል እንክብካቤ ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሂርጳ በበኩላቸው፤ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከግብርና ምርምር ማዕከላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የግብርና ምርምር ማዕከላቱ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሽታን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን በምርምር በማፍለቅ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግና ሙያዊ እገዛ የመስጠት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ለአብነት ጠቁመዋል።
ለዚህም ከዘር በፊት የሚደረግ የማሳ ዝግጅት ላይ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን፣ ቡቃያውን ከአረሞች፣ ተባዮችና በሽታዎች ቀድሞ መለየትና መከላከል ላይ በቅንጅት በመስራት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የግብርና ምርምር ማዕከላት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026