የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይልን በመጠቀም በአፍሪካ ወደ አረንጓዴ ትራንስፖርት ለሚደረገው ሽግግር ግንባር ቀደም ሆና እየሰራች ነው

May 25, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የታዳሽ ኃይል ምንጭ በመጠቀም በአፍሪካ ወደ ንጹህና አረንጓዴ ትራንስፖርት የሚደረገውን ሽግግር በግንባር ቀደምትነት ለመምራት እየሰራች መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ አረንጓዴ፣ዘላቂ እና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢ-ሞቢሊቲ) ሥርዓት የሚያሸጋግር ብሄራዊ የኢ-ሞቢሊቲ ስትራቴጂና የትግበራ እቅድ ይፋ ማድረጊያ መርሃግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃግብሩ ላይ ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተወካዮችና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ አዲሱ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የትራንስፖርት ዘርፍ በዘመናዊ መልክ ለመቅረጽ የሚጠቅም ነው ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ንጹህ ከተሞችን መፍጠር እና የህዝብ ጤናን ማሻሻል፣ ለነዳጅ ግዢ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መቆጠብ፣ የሀገሪቱን የኃይል ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችል ምህዳርን መገንባት እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

ይህ ስትራቴጂ የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን፣ የኃይል መሙያ ጣቢያዎች ግንባታን፣የህዝብ ትራንስፖርትን በኤሌክትሪክ መተካትን፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግና የግል ባለሀብቶችን ተሳትፎ ማሳደግን ያካተተ ግልጽ ፍኖተ-ካርታ የያዘ ነው ብለዋል።

የኢ-ሞቢሊቲ ሽግግር የአንድ ተቋም ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የጋራ ሀገራዊ ጥረትን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው፤ የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ የግሉ ዘርፍም ኢንቨስትመንትን እንዲያሳድጉና መሰረተ-ልማቶችን እንዲያስፋፉ ጥሪ አቅርበዋል።


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ወጪንና በነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንሱ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ገበያ የካርቦን ልቀትን መመዝገብ አስገዳጅ እየሆነ በመምጣቱ፣ አረንጓዴ ልማት ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን በገበያ ውስጥ በዘላቂነት ለመቆየት ወሳኝ መስፈርት መሆኑን አብራርተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ምርትና መገጣጠምን በማሳደግ በ2030 የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻን ሰላሳ በመቶ ለማድረስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ የባትሪ ስነ-ምህዳር እና ሰርኩላር ኢኮኖሚ መዘርጋት፣የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት፣ ጥራትን ለመጠበቅ አስገዳጅ የሆኑ ብሄራዊ ደረጃዎችን መተግበር እንዲሁም ለባትሪ ምርት ወሳኝ የሆኑትን ማዕድናት ክምችት ጥናት ማፍጠን የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በርካታ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ያሉ ማዕድናትን ተጠቅመው በሊቲየም ባትሪ ማምረቻ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን ጠቅሰው፤ የግሉ ዘርፍ በተዘጋጁት ማበረታቻዎችና የቴክኖሎጂ ፓርኮች በመጠቀም በዘርፉ እንዲሰማራ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የልህቀት ማዕከላትን ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ-ልማት ልማት ዲቪዢን ዳይሬክተር ሮበርት (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዓለም አቀፍና በአፍሪካ ደረጃ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም በፍጥነት እያደገ መሆኑንና ኢትዮጵያም በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት እየመራች መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይህ የኢ-ሞቢሊቲ ሽግግር ከልቀት ነፃ የሆኑ ከተሞችን ከመፍጠር ባለፈ፣በነዳጅ ምርቶች ሳቢያ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት ለኢኮኖሚው ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአባል ሀገራትን የኢ-ሞቢሊቲ ጉዞ ለመደገፍ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ከተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ጋር በመሆን የአፍሪካን የኢ-ሞቢሊቲ አህጉራዊ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ማድረጉን አስታውቀዋል።

ይህንን አህጉራዊ ማዕቀፍ ወደ ሀገራዊ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ መዘጋጀቱንና የ2026 የአፍሪካ ኢኮኖሚ ሪፖርትም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በምጣኔ ሀብት ሽግግር ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ በጥናት መተንተኑን ጠቁመው፣ ኮሚሽኑ የኢትዮጵያን የኢ-ሞቢሊቲ ሽግግር ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026