የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ባሕር ዳር ለነዋሪዎቿ ምቹ ለዓለምአቀፍ ጎብኚዎች ደግሞ ተመራጭ የቱሪስት ከተማ እየሆነች ነው - ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው

May 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ ባሕር ዳር በኮሪደር ልማት ለነዋሪዎቿ ምቹ ለዓለምአቀፍ ጎብኚዎች ደግሞ ተመራጭ የቱሪስት ከተማ እየሆነች ነው ሲሉ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።

የባሕር ዳር ከተማን ውበትና ፅዳት በመጠበቅ ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ደግሞ ተመራጭና ረጅም ጊዜ የሚቆዩባት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተቀረጸው ዕቅድ በተግባር እየተተረጎመ ይገኛል።

​የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት፣ ይህንን ግብ ለማሳካት የተቋቋመው የስማርት ባህርዳር ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት መሪነቱን በመውሰድ የኮሪደርና የጣና ዳርቻ ልማቶችን ሌሊትና ቀን በከፍተኛ ፍጥነት እያከናወነ ነው።


​የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ የጣና እና የዓባይ ዳርቻ ፕሮጀክቶች

​የከተማዋ ተፈጥሯዊ ሀብቶች የሆኑትን የጣና ሐይቅንና የዓባይ ወንዝን ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶታል ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት በሐይቁ ዳርቻ ላይ ዘጠኝ የሚደርሱ ቦታዎች መልማታቸውን ጨምረው አስታውቀዋል።

ይህም ከተማዋ፣ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ከሐይቁ ጋር ያላቸውን መስተጋብር በእጅጉ አሳድጎታል ብለዋል።

ከዚሁ ልማት ጋር ተያይዞም የዘንባባ ፓርክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ የከተማዋን ውበት ይበልጥ እንዳደመቀው ገልጸዋል።

​የኮሪደር ልማቱ ​የከተማዋን ዋና ዋና መስመሮች እያደሰ ያለው የኮሪደር ልማት ከደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ እስከ ዓባይ ማዶ ባለው ዋና መንገድ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።


ይህ መሠረተ ልማት ከ5 እስከ 7 ሜትር የሚደርስ ሰፊ የእግረኛ መንገድ፣ እስከ 4 ሜትር ስፋት ያላቸው ውብ አረንጓዴ መናፈሻዎች፣ ​እስከ 3 ሜትር ስፋት ያለው የተለየ የብስክሌት መንገድ፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የሕዝብ ማረፊያዎችና የሕፃናት መጫወቻዎች ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

​በተጨማሪም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እስከ ፓፒረስ ሆቴል ድረስ ያለው የእግረኛ መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝም አንስተዋል።

በከተማዋ የዓባይ ወንዝን ዳርቻን ለማልማት መታቀዱንም ነው የጠቆሙት።

​የከተማዋ የኮሪደር ልማት ዕቅድ ሲቀረጽ ጀምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌደራል መንግሥቱ ፕሮጀክቱን በመገምገምና አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የላቀ የመሪነት ሚና መጫወታቸውንም አስረድተዋል።

​ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ ተገኝተው የልማት ሥራዎቹን መገምገማቸውንና ለቀጣይ ተግባራት አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም ነው ያነሱት አቶ ጎሹ እንዳላማው።


ለኮሪደር ልማቱ ስኬት የከተማዋ ነዋሪዎችና ባለሀብቶች በገንዘብና በሐሳብ እያደረጉት ያለው ተሳትፎ አይተኬ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026