የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ከተማዋን ከጣና ውበት ጋር በማሰናሰል የተገነባ ዘመን ተሻጋሪ የቱሪዝም ሃብት ነው

Jun 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር ፤ግንቦት 27/2018 (ኢዜአ) ፡-የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ከተማዋን ከጣና ውበት ጋር በማሰናሰል የተገነባ ዘመን ተሻጋሪ የቱሪዝም ሃብት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

‎‎ከተማዋ በተፈጥሮ የታደለችና አባይና ጣናን ተንተርሳ መመስረቷ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ይበልጥ ውበቷ እየተገለጠ እንድትመጣ አድርጓታል።

የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ትዕግስት አበጀ፤ ባህር ዳር ከተማ በተፈጥሮ የታደለች መሆኗን ተከትሎ ባለፉት ጥቂት አመታት ደግሞ ውበቷን የገለጡ የልማት ስራዎች መከናወናቸው ውበቷን ያጎላው መሆኑን ገልጸዋል።


በከተማዋ ከኮሪደር ልማቱ በተጨማሪ የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው ውበቷና ድምቀቷ ይበልጥ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

የባህር ዳር የኮሪደር ልማት ከጣና ሃይቅ ጋር በተሳሰረ መልኩ የተገነባ መሆኑም ከተማዋን ልዩ ገፅታ ስለማጎናፀፉ አንስተዋል።

እንደ አጠቃላይ የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ከተማዋን ከጣና ውበት ጋር በማሰናሰል የተገነባ ዘመን ተሻጋሪ የቱሪዝም ሃብት መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ ወጣት ደጀኔ አለምነው፤ የባህር ዳር ውበትና የቱሪዝም መስህብነት ከእለት ወደ እለት እያደገ መሆኑን ተናግሯል።


‎በከተማዋ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ የተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የእግረኛ፣ የሳይክል መንገዶችና ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራቶች መዘጋጀታቸው ከተማዋን ለነዋሪዎችና ለቱሪስቶች ምቹ አድርጓታል ብሏል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ገብረስላሴ ሳህሌ፤ ከባህር ዳር ከተማ ለዘመናት ተከልሎ የነበረው የጣና ሃይቅ ውበት በኮሪደር ልማት መገለጡ ለነዋሪዎችም ይሁን ለጎብኝው ደስታ ፈጥሯል ብለዋል።

‎አሁን ላይ ወደ ባህር ዳር ጎራ የሚል ሁሉ ከተማዋን እየጎበኙ የጣናን ውበት እያደነቁ የሚደሰቱበት ስለመሆኑ ተናግረዋል።


ባለፉት ጥቂት ዓመታት በባህር ዳር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎችም የተገነቡ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026