🔇Unmute
ባህር ዳር፤ ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ለማር ምርት እድገት አስተዋጾ ማድረጉ ተገለጸ።
በክልሉ ባለፉት አስር ወራት 33 ሺህ ቶን ማር መመረቱ ተመላክቷል።
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ የንብና ሀር ልማት ባለሙያ አቶ ሙሀመድ ጌታሁን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በክልሉ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ለማር ምርት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በመርሃ ግብሩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንዱ የንብ ማነብ መሆኑን ጠቁመው በዘርፉ ከ500 ሺህ በላይ አባወራዎች፣ የተደራጁ ወጣቶችና ሴቶች እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል ።
በበጀት አመቱ አስር ወራት የንብ መንጋ ከያዙ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዘመናዊ፣ የሽግግርና ባህላዊ ቀፎዎች 33 ሺህ ቶን ማር መገኘቱን አስታውቀዋል።
የተገኘው የማር ምርት በበጀት አመቱ ለማምረት ከታቀው በላይ መሆኑን ጠቁመዋል ።
የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ትግበራ ለንብ ማነብ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ ለማር ምርት እድገት አስተዋጾ ማድረጉን አመልክተዋል።
በዘርፉ የገበያ ትስስር በመፍጠር የአናቢዎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዋግ ኽምኸራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሀና ወረዳ ቀበሌ 01 ነዋሪ አርሶ አደር አለባቸው በላይ እንዳሉት፣ በ21 ዘመናዊና በ26 ባህላዊ ቀፎዎች በመታገዝ በንብ ማነብ ስራ ተሰማርተዋል።
ዘንድሮ 410 ኪሎ ግራም ማር አምርተው በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን በሸበል በረንታ ወረዳ የመዝን ኪሮስ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ላቃቸው ደግዋለ በበኩላቸው በ42 ዘመናዊና ባህላዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እያከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።
ዘንድሮ እስካሁን ያመረቱን ከ170 ኪሎ ግራም በላይ ማር ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026