🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የተሰማሩ ዜጎች በምግብ ራሳቸውን ከመቻልና የኢኮኖሚ አቅማቸውን ከማሳደግ ባለፈ፣ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን በመዲናዋ የሚገኙ የመርሃ-ግብሩ ተጠቃሚዎች የሚናገሩት እውነታ ነው።
የሌማት ትሩፋት በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በጥቅምት 2015 ዓ.ም የተጀመረ ሀገር አቀፍ የልማት መርሃ-ግብር ነው።
መርሃ-ግብሩ ዜጎች በጓሯቸው በማምረት የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉና በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ረገድ ትልቅ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል።
ኤዜአ ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ የመርሃ-ግብሩ ተጠቃሚዎች እንደገለጹት፤ በሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ላይ በመሰማራት ውጤታማ መሆን ችለዋል፤ በዚህም አልፈው ለገበያ የምርት አቅርቦት መጨመር አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ናቸው።
የመርሃ-ግብሩ ተጠቃሚ የሆነው ሰለሞን ደሳለኝ በዶሮ እርባታ ዘርፍ በመሳተፍ በቀን ከ3 ሺህ በላይ እንቁላል በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህ መርሃ-ግብር በመታገዝ ራሱንና ቤተሰቡን መደገፍ ከመቻሉ ባሻገር፣ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አብራርቷል።
በየጊዜው በመንግስት የሚደረግለት ሙያዊ ድጋፍ በዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ እገዛ እንዳደረገለትም ነው የተናገረው።
በኮልፌ ክፍለ ከተማ በእንስሳት እርባታና በወተት ምርት ላይ የተሰማራው ወጣት ሰለሞን ደሳለኝ፤ በዘርፉ በመሰማራቱ ውጤታማ በመሆን ከራሱ አልፎ ቤተሰቦቹን ለመደገፍም በቅቷል።

በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 400 ሊትር ወተት በማምረት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሶ፣ የሚያመርቱትን የወተት ምርትም ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ መሆኑን አስታውቋል።
በመርሃ-ግብሩ በአሁኑ ወቅት በርካታ ዜጎች ተሳትፈውበት በምግብ ራሳቸውን ከመቻል አልፈው፣ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ እያስገኙ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ግብርና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መሀመድ ልጋኒ፤ መርሃ-ግብሩ የኑሮ ውድነትን በመቅረፍ፣ ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ለመገንባት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ያለው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ዜጎችን በምግብ ራሳቸውን ከማስቻል ባለፈ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ለማህበረሰቡ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታዎችን እያስገኘ መሆኑን አንስተዋል።
በመዲናዋ በርካታ ዜጎችን በመርሃ ግብሩ በማሳተፍ በየቀኑ እስከ 3 ሚሊዮን እንቁላል እንዲሁም በየዓመቱ ከ90 ሚሊዮን ሊትር በላይ ወተት እየተመረተ ነው ብለዋል።
በተለይም ቁጥራቸው ከፍተኛ ለሆኑ ወጣቶች በዶሮ እርባታ፣ በወተትና በማር ምርት ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድልና አዳዲስ የገቢ ምንጮችን እየተፈጠረ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም መርሃ-ግብሩ የተመጣጠነና ጤናማ የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦችን በቅርበትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ፣ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም የዋጋ ንረትን እያረጋጋ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ዱራሜ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርና ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችን ለልማት በማዋል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥ...
Jun 6, 2026
ደሎ መና፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የአርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያግዙ ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ...
May 26, 2026
ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክ...
May 21, 2026
አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...
Apr 29, 2026