የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ምሩቃን የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተለያዩ ዘርፎች ስራ ፈጥረው ኢኮኖሚውን ሊደግፉ ይገባል

Jun 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ ተመራቂዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተለያዩ ዘርፎች ስራ ፈጥረው ኢኮኖሚውን ሊደግፉ እንደሚገባ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር) ገለፁ።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 843 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።


የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር)፤ ምሩቃን ተማሪዎች የተለያዩ ውጣ ውረዶችን አልፈው ለዛሬ ምርቃት በመብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በቆይታቸው ያገኙትን እውቀት፣ ልምድና ክህሎት ተጠቅመው ሀገርና ህዝባቸውን በእኩልነት፣ በታማኝነትና በቅንነት ሊያገለግሉ ይገባል ብለዋል።

ምሩቃን ስራ ፈጣሪ እንጅ ስራ ፈላጊ እንዳይሆኑ ያሳሰቡት ፕሬዚዳንቱ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቅመው በተለያዩ ዘርፎች ስራ ሊፈጥሩና ኢኮኖሚውን ሊደግፉ ይገባል ብለዋል።

በሚሄዱበት አካባቢና በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም እንዲሰሩም አመልክተዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳና የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በበኩላቸው፣ ምሩቃን በቆይታቸው ያገኙትን ልምድና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ህዝብና ሀገር ሊያገለግሉ ይገባል ብለዋል።


የዛሬው ምርቃት የድል መጀመሪያ እንጅ መጨረሻ አለመሆኑን ተረድተው በቀጣይም እውቀትና ክህሎታቸውን በማሳደግ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ትግበራ ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ታላቅ ህልምና ራዕይ ሰንቀው፣ ስነ ምግባራቸውን ጠብቀው፣ በታማኝነት የህብረተሰብ አገልጋይ እንዲሆኑም መክረዋል።

ተመራቂዎች ችግርና ፈተናዎችንም ወደ እድል በመቀየር የጀመሩትን የስኬት ጉዞ ሊቀጥሉ እንደሚገባ አመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።


በእንሰሳት ህክምና ተመራቂዎች መካከል ተመስገን አሊ በሰጠው አስተያየት፤ በቆይታው ያገኘውን እውቀትና ክህሎት ተጠቅሞ በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይም የደሴ ከተማና የወሎ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የተማሪ ወላጆችና ቤተሰቦችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026