የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኤን ቢ ሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦

Jul 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ከቱሪዝም መሠረተ-ልማት ጋር በተያያዘ አበረታች ሥራዎች ተሠርተዋል። በተለይም በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል፤ አሁንም እየተከናወኑ ያሉና በቅርቡ የሚመረቁ አሉ።

ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰባት የአውሮፕላን ማረፊያዎችን አስመርቀናል። በተጨማሪም በርካታ መንገዶች ተገንብተዋል። ይህም ለቱሪዝሙ ከፍተኛ መነቃቃት ይፈጥራል።

የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ (ፕራይቬት ሴክተር) በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ግብ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ አሁን ለመጣው የቱሪዝም መነቃቃትና ሥራ የማይተካ ሚና ተጫውቷል።

ቱሪዝም ቅርስ ብቻ አይደለም፤ ቅርስ ስላለ በቀጥታ ቱሪዝም ይሳባል ማለት አይደለም። ቱሪዝም የተፈጥሮ ሀብት ብቻም አይደለም። ቱሪዝም ሸመታ ከሌለው በሴክተሩ የገንዘብ ልውውጦች (ትራንዛክሽን) ከሌለው የቱሪዝም ኢኮኖሚ ሊባል አይችልም።

ቱሪዝም በአጭሩ ሊጎበኘን የመጣ ሰው ልቡ ተደስቶ፤ ኪሱ ተራቁቶ መሄድ አለበት ማለት ነው።

ከፕሮሞሽን አንጻር ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል። ብዙ የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚቀረን እኛም እናውቃለን፤ ወዳጆቻችንም ይነግሩናል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያን አስውቦ፣ አሳምሮ፣ አልቆ የመሥራት ብቻ ሳይሆን የመግለጥ ኃላፊነት አለበት። ሀገራችንን ማስተዋወቁን በተቀናጀ መንገድ ስንሠራ የምናገኘውም ጥቅም በዚያው ልክ እያደገ ይሄዳል።

በሚሠሩት ሥራዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅርስ ይጠፋብኛል ብሎ ይሰጋል ብዬ አላምንም። እንደዛ ዓይነት ስጋት አላይም።

በዚህ ዓመት 10 ነጥብ 2 ጂ ዲ ፒ ዕድገት እንጠብቃለን። ይህ ዕድገት በኢትዮጵያ ብቻ እንጅ በድፍን አፍሪካ የለም።

በዚህ ዓመት ከ10 ነጥብ 8 እስከ 11 ቢሊየን ዶላር ኤክስፖርት እናደርጋለን። ይህ ከሁለት/ሦስት ዓመት በፊት ሦስት ቢሊየን ዶላር የነበረ ነው።

በዚህ ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ጎብኚተዋል። ይህ ቁጥር ከካች አምናው አንጻር የ300 ሺህ እንዲሁም ካለፈው ዓመት አንጻር የ100 ሺህ ቱሪስቶች ቁጥር ጭማሪ አለው። ከውጭ ሀገራት ጎብኚዎችም (ማይንስ ተጨምሮ) ዘንድሮ ከ 5 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ 50 ነጥብ 16 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተለያዩ የሀገራቸውን ክፍል ጎብኝተዋል። ይህ አሃዝ ከታች ዓምናው አንጻር በ9 ነጥብ 4 ሚሊየን እንዲሁም ካለፈው ዓመት አንጻር በ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብልጫ አለው።

ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ከ79 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

በዚህ ዓመት 204 ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ተካሂደዋል። ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት አንጻር የ50 ኮንፈረንሶች ብልጫ አለው። ከካች አምና አንጻር የ166 ኮንፈረንሶች ብልጫ አለው።

በዚህ ዓመት ለማይንስ (ኮንፈረንስ) ቱሪዝም ብቻ ከ166 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ትሰበስባለች። ከለውጡ በፊት 200/300 ሺህ ብር ነበር ዓመታዊ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026