የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Jul 31, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦‎ የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ሀገር በቀል ሆኖ በሰባት አምዶች ተደራጅቶ የተቀረጸውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር አፈጻጸም ሪፖርት ለሪፎርም ምክር ቤቱ ቀርቦ በዝርዝር ተገምግሟል ብለዋል።

አምዶቹም ዘመኑን የዋጀና በተዋረድ የተናበበ አደረጃጀት፣ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ብዝሃነት፣ ዲጂታላይዜሽ፣ የለውጥ አመራር እና የአገልግሎት ማሻሻያን የያዘ መሆኑን ገልጸዋል።


አፈጻጸሙም ፍጥነትን፣ ፈጠራን፣ ፈጻሚዎቹን ባለቤት ማድረግንና ዘላቂ ሥርዓት ግንባታን መሠረት ተደርጎ በጥብቅ ዲስፕሊንና በእውቀት ውጤታማ እና ተስፋ በሚሰጥ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑንም አይተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

በሪፖርቱ ሰው ተኮር በሆነ ሁኔታ የመሶብ አገልግሎትን በማስፋፋት ሂደት ጉልህ የሚባል መሻሻል በየከተሞቹ ታይቷል ሲሉም አስታውቀዋል።

በመልዕክታቸው አክለውም በአገልግሎት ማሻሻያ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የምንችል መሆኑንና በዜጎች በኩል የነበረውን እሮሮ መፍታት መጀመራችን በተግባር የታየበትም ጉዳይ ነው ብለዋል።

የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋለ።

ለዚህም ሥራ የጠራ መረጃ ማደራጀት፣ ቴክኖሎጂን ማበልጸግና የሰራተኞችን ብቃት ማጠናከር የቀጣይ ትኩረት እንዲሆን በምክር ቤቱ አቅጣጫመቀመጡንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉራጌ ዞን በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም  ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው

ወልቂጤ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ በፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ልማት ላይ መሰማራታችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ አስችሎናል ሲሉ የጉራጌ ዞን አርሶ ...

Jul 29, 2026

አፍሪካ የራሷን ዘላቂና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ በመገንባት ዓለም አቀፍ ተደማጭነቷን ማጎልበት አለባት

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የራሷን ዘላቂና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ በመገንባት ዓለም አቀፋዊ ተደማጭነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን ማጎልበ...

Jul 29, 2026

በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል

ዲላ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ እንደሚጠ...

Jul 16, 2026

የሩዝ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል

መቱ ፤ ሐምሌ 2/ 2018(ኢዜአ):- የሩዝ ልማት ስራ ላይ መሳተፋችን ምርታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ አስችሎናል ሲሉ በኢሉባቦር ዞ...

Jul 10, 2026