የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ81 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ ሰብል እየለማ ነው

Jul 31, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጊምቢ፣ሐምሌ 24/2018(ኢዜአ)፦በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ81 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ ሰብል በመልማት ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።


ምዕራብ ወለጋ ለበቆሎ ምርት ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት፣ ለም አፈር እና በቂ የዝናብ ስርጭት ያለው አካባቢ ነው።


የበቆሎ ሰብል ለአካባቢው አርሶ አደሮች ዋና የምግብ ምንጭ ከመሆኑ ባሻገር ለገበያ በመቅረብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚፈጥር ሰብል ነው።


ይህንን ሰፊ መሬት በበቆሎ ለመሸፈን አስቀድሞ የመሬት ዝግጅት ከተከናወነ በኋላ ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ እና የፀረ-ተባይ መድሃኒቶች ለአርሶ አደሩ ቀርቦ ከ81 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ ሰብል መልማቱ ነው የተገለጸው።


የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም የምርት ሂደቱን እና የሰብል እንክብካቤውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸው እንዲሁ።


የምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፈይሣ ሀምቢሳ እንደገለጹት፥ የበቆሎ ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ እንዲያርሱ እየተደረገ ነው።


አክለውም፣ ለዘመኑ እርሻ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የግብርና ግብዓቶች በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እንዲቀርቡና ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረጉን አመልክተዋል።


በተለይም የዘንድሮ የአየር ሁኔታ ለቦቆሎ ሰብል አመቺ በመሆኑ የተሻለ ምርት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።


በዚህም በበቆሎ ሰብል እየለማ ካለው 81 ሺህ 244 ሄክታር መሬት ከ3 ሚሊዮን 845 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኃላፊው አመልክተዋል።


በዞኑ በበቆሎ ሰብል ልማት ላይ ከተሰማሩት አርሶ አደሮች መካከል የቤጊ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብዱላሂ ሙሐመድ አንዱ ናቸው።


አርሶ አደሩ ከግብርና ባለሙያዎች በሚያገኙት ሙያዊ ምክር እና ባላቸው የቆየ ልምድ በመታገዝ፣ አንድ ሄክታር መሬታቸውን በበቆሎ ሰብል ሸፍነው አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።


ከዚህ ቀደም ከአንድ ሄክታር ከ30 ኩንታል ያልበለጠ ምርት ያገኙ እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሩ፣ ዘንድሮ ግን እስከ 40 ኩንታል የበቆሎ ምርት ለማግኘት የሚያስችሉ አስፈላጊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።


በየዓመቱ በስፋት የበቆሎ ሰብል እንደሚያለሙ የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው አርሶ አደር አቶ ደቤላ ዲንሳ ናቸው።


አርሶ አደሩ አክለውም፣ በዘንድሮው የምርት ዘመን በአንድ ሄክታር መሬታቸው ላይ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ የበቆሎ ሰብል በማልማት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።


የዘንድሮው የአየር ሁኔታ ለምርት ሂደቱ አመቺ በመሆኑ፣ የተሻለ ምርት ለማግኘት ሙሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው መዝራታቸውን አርሶ አደሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጉራጌ ዞን በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም  ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው

ወልቂጤ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ በፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ልማት ላይ መሰማራታችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ አስችሎናል ሲሉ የጉራጌ ዞን አርሶ ...

Jul 29, 2026

አፍሪካ የራሷን ዘላቂና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ በመገንባት ዓለም አቀፍ ተደማጭነቷን ማጎልበት አለባት

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የራሷን ዘላቂና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ በመገንባት ዓለም አቀፋዊ ተደማጭነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን ማጎልበ...

Jul 29, 2026

በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል

ዲላ፤ ሐምሌ 8/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ሥራ እንደሚጠ...

Jul 16, 2026

የሩዝ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል

መቱ ፤ ሐምሌ 2/ 2018(ኢዜአ):- የሩዝ ልማት ስራ ላይ መሳተፋችን ምርታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ አስችሎናል ሲሉ በኢሉባቦር ዞ...

Jul 10, 2026