የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም ትልልቅ የኢኮኖሚ ውሳኔዎችና አዳዲስ አሰራሮች የሚመላከቱበት መድረክ ነው

Sep 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም ትልልቅ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ጉዳዮች የሚዳሰሱበትና አዳዲስ አሰራሮች ይፋ የሚደረጉበት አህጉራዊ ተጽዕኖ ያለው ጉባዔ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 በዐድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በኢኮኖሚውና በፋይናንስ ዘርፉ የተወሰዱ ወሳኝ የፖሊሲ እርምጃዎችን፣ የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎችን፣ የባንኮችን እንቅስቃሴ እንዲሁም የዋጋ ግሽበትንና ሀገራዊ ግቦችን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቅ፣ ትልልቅ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ጉዳዮች የሚዳሰሱበትና አዳዲስ አሰራሮች ይፋ የሚደረጉበት አህጉራዊ ተጽዕኖ ያለው ጉባዔ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የሶስተኛውን ዙር የፋይናንስ ተደራሽነት ስትራቴጂ ይፋ መደረጉን ጠቅሰው፤ የሀገሪቷ ን የክፍያ ስርዓት ከአፍሪካ አህጉራዊ የክፍያ ስርዓት (PAPSS) ጋር የማገናኘት ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ተቀዳሚና ዋና ተግባር የዋጋ መረጋጋትን እንዲሰፍን ማድረግ መሆኑን ያረጋገጡት ገዢው፤ የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

የዋጋ መረጋጋትን መፍጠርና የዋጋ ግሽበትን መቆጣጣር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል አንዱ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዚህ ውጤት የሚለካው በዜጎች የገቢ እድገት፣ እንዲሁም እንደ ምግብና የቤት ኪራይ ባሉ መሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ መቀነስ መሆኑን አስረድተዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገኘውን የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ ስኬት በሚመለከት፣ ሌሎች ሀገራት በ10 ዓመታት ያሳኩትን ውጤት ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ በኦፊሴላዊው እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ጠቦ አንድ ገበያ (Converge) እንዲፈጠር ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ባንኮች እርስ በእርሳቸው የውጭ ምንዛሬ መበዳደርና መነጋገር የሚያስችላቸው የኢንተር ባንክ ኤፍ ኤክስ ማርኬት ስርዓት መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ የተደራጀ ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አመልክተው፤ ብሔራዊ ባንክ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለጨረታ ማቅረቡንና ይህን አቅርቦቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026