የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ነው 

Oct 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሸገር ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላቱ ለኢሬቻ በዓል አከባበር ወደ ሀገር ቤት የመጡ ሲሆን፣ በሸገር ከተማ በሚገኘው የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው።

የዲያስፖራ አባላቱ በኢንስቲትዩቱ በተከናወኑ የዲጂታል ልማት ስራዎቹ መደመማቸውንም ገልጸዋል።


ከአሜሪካ የመጡት ዶክተር ተመስገን ሻሾ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተመለከቱት ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለተተኪው ትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው።

"ዓለም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እየተደገፈች ያለችበት ወቅት በመሆኑ፣ ሀገራችን ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከውጭ ይገቡ የነበሩ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የጀመረችው እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታ ነው" ብለዋል።


በተለይም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንዲደገፉና ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራውን ስራ ያደነቁት ዶክተር ተመስገን፤ አሁን የተጀመሩት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ በተሻለ የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ተመስገን፤ በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራቸው መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የልማቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


ከደቡብ አፍሪካ የመጡት አቶ ኡመር ኡስማን በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩቱ ባዩት ስራ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚከናወኑት ተግባራት ትውልዱ በሀገሩ ሰርቶ እንዲለወጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል።

በኦሮሚያ ክልል በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ አስተማማኝ አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያመላክት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

ሀገሪቱ በአስተማማኝ የዕድገት መስመር ላይ የምትገኝ መሆኗን በመጠቆም፣ ዲያስፖራው በሀገሩ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።


በተመሳሳይ ከኖርዌይ የመጡት ወይዘሮ ሌንሴ ለሜሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ወጣቶች በሀገራቸው ጥራት ያለው ትምህርት አግኝተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዲማ እንዳሉት፤ ጉብኝቱ በየዓመቱ በኢሬቻ ሳምንት በክልሉ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት ባህል አካል ነው።


አክለውም በኢንስቲትዩቱ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰልጥነው ለነገዋ ሀገር ተስፋ የሚሆኑበትን አሰራር መመልከታቸው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሚን ጁንዲ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እስካሁን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከ200 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።


ይህም ከፍተኛ የዕውቀት ብቃት (IQ) ያላቸውን ተማሪዎች በማፍራት ሀገራቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ስራ መሆኑን ያብራሩት አቶ አሚን፤ የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በሀገራችን እየመጣ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ በተግባር በማሳየት አባላቱ ሀገራቸውን በዕውቀትም ሆነ በኢንቨስትመንት ለመደገፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026