የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የካፒታል አቅሙን በማጎልበት የዘርፉን ደህንነት ለማስጠበቅ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ነው

Oct 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የካፒታል አቅሙን በማጎልበት የተቀማጭ ገንዘብና የፋይናንስ ሥርዓቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በሰነቀችው ኢትዮጵያ ሁለተኛው የፋይናንስ ፎረም 2026 የዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱን ቀጥሏል።

ከመስከረም 19 እስከ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ አቅም ለማሳደግና የባለድርሻ አካላትን ትብብር ለማጠናከር ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል።

"ተቀማጭ ገንዘብን መጠበቅ፣ እምነትን መገንባት እና የፋይናንስ መረጋጋትን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት ትናንት ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር መርጋ ዋቅወያ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ የፋይናንስ ሥርዓቱን ደህንነትና የተቀማጭ ገንዘብን በአስተማማኝነት መጠበቅ የሚያስችለውን የፋይናንስ አቅም እየገነባ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት ተቋሙ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብና የሀብት አስተዳደር ስልቶቹን በማጠናከር የካፒታል መጠኑን በማሳደግ ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን አስታውቀዋል።

ይህ የተገኘው ዕድገት የፋይናንስ ዘርፉን ደህንነትና መረጋጋት ለማረጋገጥ እንዲሁም የሕዝብን እምነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ተቋሙ የካፒታል መሠረቱን የበለጠ በማጠናከርና ዘመናዊ የአሠራር ስልቶችን በመተግበር ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታደሰ ሃቲያ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ መቋቋም ለጠቅላላው የፋይናንስ ተቋማትና ለዘርፉ ደህንነት እጅግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል።

ተቋሙ ለባንኮች ዕድገት የጽናት መሠረት በመሆኑ፣ ከተቋሙ ጋር በቅርበትና በትብብር መሥራት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የተቋሙ መኖር ለባንክ ደንበኞችና ለኅብረተሰቡ የሚሰጠው ዋስትና ከፍተኛ በመሆኑ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመው ባንኩ ይህንኑ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ማኅበር (AEMFI) ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ከበደ፣ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸው ተግባራት ተስፋ ሰጪ ናቸው ብለዋል።

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የዚህ ፈንድ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፣ በቀጣይ ከፈንዱ ጋር ያላቸውን ቅንጅታዊ አሠራር እና ትብብር ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ለማኅበሩ አባል ተቋማት ስለ ፈንዱ ጥቅም፣ አሠራርና ጠቀሜታ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፣ በቀጣይ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ለመሥራት ማኅበሩ ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል።

በሆርን የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት (HESPI) የጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር ገብረሕይወት አገበ (ዶ/ር) የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው የሚሠራበትና በኢትዮጵያም መቋቋሙ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ተቋሙን ይበልጥ ለማጠናከር የሁሉም ወገኖች ኃላፊነትና ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ተቋሙ ውጤታማ እንዲሆንና ከፖሊሲ እንዲሁም ከሌሎች ዘርፎች ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናትና ምርምር ለመቅረፍ በትኩረት መሠራት እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026