የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የክልሉን ሁለንተናዊ ልማትና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ርዕሰ መስተዳድር  ኦርዲን በድሪ 

Oct 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀረር፣መስከረም 22/2019 (ኢዜአ):- በሀረሪ ክልል በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የክልሉን ሁለንተናዊ ልማትና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መስራች ጉባዔውን እያካሄደ ሲሆን አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በክልሉ ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

በዚህም ህዝቡንና ክልላችንን ወደ ከፍታና ብልፅግና ለማድረስ መንገድ ጀምረናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በፖለቲካ ፣ በሰላም፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር ፣የትምህርትና ጤና አገልግሎት ጥራት እንዲረጋገጥ መደረጉን ጠቁመው በኮሪደር ልማትም ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል።

የሀረር ከተማን በዓለም አቀፍ መድረኮች እውቅና እንድታገኝ ከማስቻል ባሻገር በግብርናና በሌማት ትሩፋት ዘርፎች ምርታማነትን በማሳደግ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የክልሉን ሁለንተናዊ ልማትና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

የተመዘገቡ ውጤቶች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ከማድረግ ባሻገር ለክልሉ እድገት የበለጠ አቅም የሚሆኑ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በዕቅድ በመያዝ ተግባራዊ እናደርጋለን ሲሉም አክለዋል።

ሀረር የሰላም ተምሳሌት እንድትሆንና በክልሉ ፈጣን፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር ይሰራል ብለዋል።

በክልሉ የማህበረሰቡን ህይወት የሚያሻሽሉ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ ክልሉን በኮሪደር ልማት ለስራ፣ ለኑሮና ለቱሪዝም ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ይሰራል ሲሉ አመላክተዋል ።

በክልሉ ፍትሀዊ የመሰረተ ልማት ስርጭት እንዲኖርና የዜጎች የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከብልሹ አሰራር የፀዱ ፣ይበልጥ ፍትሀዊና ፈጣን እንዲሆኑ በማስቻል የዜጎችን እርካታ ለመጨመር ይሰራል ሲሉም አስታውቀዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026