የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የግብፅ አስዋን ግድብ የጥፋት ውርስ-የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እንደጻፉት

Oct 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

የግብፅ አስዋን ግድብ በአፍሪካ አወዛጋቢ ከሆኑ የሜጋ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው። የግድቡ መገንባት ከ100 ሺህ በላይ ኑቢያውያንን ከቀያቸው፣ ከህይወታቸውና ከመሬታቸው አፈናቅሏል፤ ለከፋ ችግር እንዲዳረጉም አድርጓል።

የአስዋን ግድብ የግንባታ ሂደት የአንድ ወገን እርምጃና የጥፋት አሻራ የተስተዋለበት ነው። ኢትዮጵያ በወቅቱ ምክክርና ውይይት እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥሪ ብታቀርብም፣ ግድቡ ግን ያለ ኢትዮጵያ ፈቃድና ስምምነት ተገንብቷል።

በአሜሪካ እና በብሪታንያ በወቅቱ የተጠኑ ሰነዶች፣ በአስዋን ግድብ ግንባታ ሂደት ላይ ከዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ሰፊ ምክክር ባለመደረጉ የነበረውን ስጋት በግልጽ ያመላከቱ ነበሩ። ከ1952 እስከ 1960 ባሉት ጊዜያት የተመዘገቡ 15 ኦፊሴላዊ መዝገቦች ይህንን ስጋት አስፍረዋል።

ነገር ግን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እ.ኤ.አ. በ2015 በተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሠረት ዘመናዊ የሕግ ማዕቀፍን ይከተላል። ግብፅ ኢትዮጵያን ከመንቀፏ በፊት፣ አስዋን ግድብን ያለ ኢትዮጵያ ስምምነት ለምን እንደገነባች እና ከ100,000 በላይ ኑቢያውያንን ለምን እንዳፈናቀለች በግልጽ ማስረዳት አለባት።

ግብፅ የአስዋን ግድብን ከየትኛውም የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ምክክር ሳታደርግ መገንባቷ፤ እንዲሁም የጉዳት ጥናት እንኳ ሳይደረግ ኑቢያውያንን ከኑራቸውና ከቀያቸው በማፈናቀል ለከፍተኛ ችግር መዳረጓ የግድቡ የጥፋት ውርስ ነው።

ኢትዮጵያ በወቅቱ ምክክር እንዲደረግ ያቀረበችው ተደጋጋሚ ጥያቄም በግብፅ በኩል መልስ አላገኘም። በተቃራኒው የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብፅ እ.ኤ.አ. በ2015 በተፈረመው የመርሆች ስምምነት መሰረት ለውይይት ተደራሽ ተደርጓል።ከዚህ አኳያ ግብፅ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያን ለመንቀፍ ምንም አይነት ሞራላዊና ምክንያታዊ መሠረት የላትም።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026