🔇Unmute
ጊምቢ፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ በመደመር መንግሥት የተተለሙት ዕቅዶች የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የተሻለች ሀገርን ለመገንባት የሚያስችሉ መሆናቸውን በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የጉሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የመደመር መንግሥት በቀጣዮቹ የሥልጣን ዘመናት ሀገራዊ ዕድገትንና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ትልልቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን ነድፎ ወደ ተግባር ገብቷል።
እነዚህ ዕቅዶች ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን፣ የከተሞች የኮሪደር ልማትን፣ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ተግባራትንና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለሙ ናቸው።
በተጨማሪም የመንግሥት አሠራርን በማዘመን፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመደገፍና የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ የዜጎችን ቀጥተኛ ተጠቃሚነት ማሳደግ የቀጣይ ጉዞው አበይት ማዕከላት ተደርገው ተይዘዋል።
ነዋሪዎቹም ለኢዜአ እንዳሉት፤ በመደመር መንግሥት የተተለሙት ዕቅዶች የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የተሻለች ሀገርን ለመገንባት የሚያስችሉ ናቸው።
በመደመር መንግሥት የተያዙ ዕቅዶች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የሀገርና የሕዝብን ተጠቃሚነት መሠረት ያደረጉ ናቸው ያሉት የጉሊሶ ከተማ ነዋሪው አቶ መርጋ ሰሳባ ናቸው።
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የኅብረተሰቡን ሕይወት የቀየሩ ተጨባጭ ሥራዎች መሰራታቸውን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በመደመር መንግሥት የተያዙት ዕቅዶች የተሻለች ሀገር ለመገንባት የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዞኑም ሆነ እንደ ሀገር መንግሥት በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስኬታማ ሥራዎችን ማከናወኑ የሚደነቅ ነው ያሉት ደግሞ አቶ አበበ መንገሻ ናቸው።
በተለይም በግብርናው ዘርፍ ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ ባሉ ኢኒሼቲቮች የሀገሪቱ ገጽታ መቀየሩን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በሁሉም የልማት ዘርፎች ለላቀ ስኬት መሠራት እንዳለበት ተናግረዋል።
አዲሱ መንግሥት የጀመራቸው የለውጥ ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ሰላምን ማጽናት እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ አቶ ጂማ ሀምቢሳ ናቸው።
የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት ዓመታት በኮሪደር ልማት፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ መሠረተ ልማትና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች የተጀመሩት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...
Sep 15, 2026
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026