🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማሳደግን ዓላማ ያደረገው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 እስክ 30 ቀን 2019 ዓም እንደሚከበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ።
ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) “ንቁ ዜጋ ደህንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለቀጣይ አንድ ወር የሚከበረውን 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በመግለጫቸው፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በፍጥነት ማደጉን ተከትሎ በዜጎች፣ በተቋማትና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃት የሚጨምርበት ሁኔታ እንደሚታይ ገልጸዋል።በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትንና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማጎልበት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።
ዘንድሮ በሚከበረው ወር የተቋማትን እና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማጎልበት ለጉዳዩ ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር በህጻናት የበይነ-መረብ ጥበቃ ላይ ትኩረት ማድረጉን አመልክተው የህጻናት የበይነ-መረብ አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከበር ተናግረዋል።
በወሩ ታዳጊዎችና ወጣቶችን የሚያሳትፍ ውድድርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሳይበር ደህንነት ላይ የውይይት መድረክ እንደሚካሄድም ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ላይ ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በመሆኑም የጥቅምት ወርን የመንግስትና የግል ተቋማት በዘርፉ የሰራተኞቻቸውን ግንዛቤ በሚያሳድጉ ተግባራት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ከጥቅምት 1 አስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ 7ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን በደመቀ ሁኔታ ማክበር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።
የሳይበር ደህንነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለሰባተኛ ጊዜ እንደሚከበርም ተመላክቷል።
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...
Sep 15, 2026