የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ይለማል

Oct 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ የበጋ መስኖ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ ለኢዜአ እንደገለጹት ዘንድሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በስፋት ይካሄዳል።

በክልሉ ዘንድሮ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት ከ160 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።

ከታቀደው መሬት እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ 400 ሺህ ሄክታር መዘጋጀቱን ጠቁመው ከዚህም ውስጥ 130 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የስንዴ ልማት ሥራዎች በሰፊው እና በተቀናጀ መልኩ ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸው ፣በዚህም አርሶ አደሩ ልምድና ክህሎት በማግኘት ከፍተኛ ተነሳሽነት እየጨመረ ነው ብለዋል።

የመስኖ የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለውጪ ገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅምን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው አቶ በሪሶ አብራርተዋል።

ልማቱ የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የመስኖ ልማቱ የሚከናወነው በገጽ እና በከርሰ ምድር የውሃ አማራጮች በመሆኑ፣ ለአርሶ አደሩ በርካታ የውሃ መሳቢያ ፓምፖች መቅረባቸውን አቶ በሪሶ አመልክተዋል ።

ከስንዴ ልማት ጎን ለጎን በመደበኛ የመስኖ ልማት መርሃ ግብር ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ገበያን ለማረጋጋት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።

ለልማቱ ስኬታማነት ለአርሶ አደሩ አስፈላጊው የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና፣ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ጠቁመው ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በበቂ ሁኔታ መቅረቡን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026