የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ሀገራዊ እድገትን እያፈጠነ ነው

Oct 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ዲላ፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ፈጣን እድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉን የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ "ወቅታዊ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና እድገቶች" በሚል ርዕስ አውደ ጥናት ተካሂዷል።


በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙ የዘርፉ ምሁራን እንዳሉት የተሟላ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እውን መሆን ፈጣን ሁለንተናዊ እድገት እንዲመዘገብ አስችሏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና ለኢዜአ እንዳሉት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ብዝሃ ዘርፎችን በማነቃቃት የሀገሪቱን የእድገት ጉዞ እያፋጠነ ነው።

በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዋጋ ንረት ሲከሰቱ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመፍታት የተሟላ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ትግበራን ውጤታማ እያደረገው መምጣቱን ጠቁመዋል።

የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያው እንዲመራ መደረጉም የዋጋ ግሽበትን በማረጋጋት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደጉን ፕሮፌሰር ጣሰው አክለው ገልጸዋል።

የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን ተከትሎ የመጣውን የኢኮኖሚ እድገት በውጫዊ ተጽኖ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳይገባ ማህበሩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን ለፖሊሲ ግብዓትነት እያዋለው ነው ብለዋል።


የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትግበራው የሀገርን ጸጋዎች በአግባቡ ለይቶ ለልማት በማዋል የነበሩ ክፍተቶችን የቀረፈ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢኮኖሚ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ታምራት በየነ (ዶ/ር ) ናቸው።

በተለይ በራሳችን መንገድ ችግሮችን የመፍታት ባህልን በመገንባት በኩል የተሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ግሽበትንና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማስተካከል ባለፈ በዲጀታል ፋይናንስ ከዓለም እኩል ለመራመድ ምቹ መደላድል መፍጠሩን የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ገልጸዋል።

በዘርፉ የተስተዋለውን እድገትና የገጠመውን ተግዳሮት በምርምር በመለየት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ውጤታማነት አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውንም ታምራት (ዶ/ር) አንስተዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ሦስት የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበርና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአቅም ግንባታና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት የሚያስችላቸው የሦስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026