🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች ያሏት ሀገር መሆኗን በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብደላ ቢን ሀሰን አል-ዛህራኒ ገለጹ።
በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው ወዳጅነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጎለበተ መምጣቱን አምባሳደሩ ከኢዜአ ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለግንኙነቱ ማደግ ያላቸው ቁርጠኝነት እና የጉብኝት ልውውጦች የትብብር መስኮችን በማስፋት ለአዲስ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በር መክፈቱን አመልክተዋል።
በቅርብ ወራት በሪያድ እና በአዲስ አበባ መካከል የተደረጉ ጉብኝቶች የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩን ተናግረዋል።
በዚህም ኢኮኖሚን ጨምሮ የሁለቱን ሀገራትና ህዝቦች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስምምነቶችን ለማጠናቀቅ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
የንግድና የኢንቨስትመንት ልውውጡን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የሁለቱ ሀገራት ኤምባሲዎች የንግድ አጋርነትን በማስፋፋት ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የግል ባለሀብቶችንና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ፍላጎት ያላቸውን አካላት ያሰባሰበ የሳዑዲ-ኢትዮጵያ የቢዝነስ ካውንስል ተቋቁሟል።
ይህ የቢዝነስ ካውንስል ባለፉት ወራት በርካታ ስብሰባዎችን ያካሄደ ሲሆን፣ በቅርቡም ሌላ ስብሰባ በማካሄድ በሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከርና አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመዳሰስ አቅዷል።
ስለ ሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ መጠን ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደሩ፤ እአአ በ2025 ሳዑዲ ዓረቢያ ከኢትዮጵያ ያስገባችው የወጪ ንግድ መጠን ወደ ሁለት ቢሊዮን የሳዑዲ ሪያል መጠጋቱን ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና 80 በመቶ ድርሻ የሚይዝ ሲሆን፣ ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው ምርት ደግሞ 184 ሚሊዮን ሪያል መድረሱንም ነው የጠቆሙት።
ሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጡን የበለጠ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸው የጠቆሙት አምባሳደሩ ይህን ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ አቅም እንዳለ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ያልተነካ ሰፊ ሀብት ያላት መሆኗን ገልጸው፤ የሳዑዲ አረቢያ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚችሉባቸው እድሎች መኖራቸውን አንስተዋል።
አምባሳደሩ በማዕድን፣ በእርሻ፣ በቱሪዝም እና በውሃ ሀብት ዘርፎች ላይ ሳዑዲ ዓረቢያ አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ አብራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል።
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...
Sep 15, 2026