🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የታዳሽ ኃይል አቅም በመጠቀም ሁለንተናዊ ዕድገቷን ለማፋጥን እየተጋች መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ልማት ማህበር ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 2ኛውን የኢትዮጵያ ታዳሽ ኢነርጂ ጉባኤ በስኬት እያካሄደ ይገኛል።

"ፈጠራን፣ ኢንቨስትመንትንና ሽግግርን በማቀናጀት የታዳሽ ኢነርጂ ሽግግርን ማፋጠን" በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው ጉባኤው፤ የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ፣ የገበያ ዕድሎችን በማስፋት እና ዓለም አቀፍ ትብብርን በመፍጠር የኢትዮጵያን የኢነርጂ ሽግግር ለማፋጠን እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በዚሁ ወቅት እንደተገለጸውም ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የታዳሽ ኃይል አቅም በመጠቀም በግብርና፣ ኢንዱስትሪና ሌሎች ዘርፎች ምርታማነትን ለማሳደግ እና የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማፋጠን በቁርጠኝነት እየሰራች ትገኛለች፡፡
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሶላር ኢነርጂ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ የምስራች ሲሳይ፤ መድረኩ ኢትዮጵያ ያላትን እጅግ ሰፊ የታዳሽ ኃይል አቅም ወደ ሁለተናዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለመቀየር ትኩረት ሰጥቶ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ጉባኤው የግል ዘርፉን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከርና ዘመናዊ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ አሊ መሐመድ በበኩላቸው፤ ታዳሽ ኃይልን ከግብርናው ዘርፍ ጋር በማቀናጀት የምርት ጥራትን ለማሻሻል በስፋት መጠቀም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ታዳሽ ኃይል የኃይል ዘርፍ አማራጭ ብቻ ሳይሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ቁልፍ መፍትሔ መሆኑን አስረድተዋል።

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ መስፍን ዳቢ በበኩላቸው፤ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ማስፋፋት የሁለተናዊ ኢኮኖሚ ለውጥ፣ የኢንዱስትሪ ልማት እና የግብርና ምርታማነት ዋና መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።
ኤሌክትሪክ ለኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽንና ለተሻሻለ የዜጎች ኑሮ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...
Sep 15, 2026