🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አሕመድ ሽዴ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከዳንጎቴ ኢንዱስትሪስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ሽያጭ ማስተዋወቂያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አሕመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮዲት ካሳ፣ የዳንጎቴ ግሩፕ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አሊኮ ዳንጎቴን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ሽያጭ ይፋ የተደረገው 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ለማሰባሰብ በማለም መሆኑም ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት አክሲዮኑ በናይጄሪያ እየተሸጠ ሲሆን ሌሎች አፍሪካዊያን ባለሃብቶች እንዲሳተፉም ዕድል ተመቻችቷል ተብሏል።
በናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ የሚገኘው የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ በአሁኑ ወቅት በቀን 650 ሺህ በርሜል ነዳጅ የማጣራት አቅሙን ወደ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለማሳደግ ግብ ተጥሏል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አሕመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ የቢዝነስ ማዕከል እያደረገ ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጭነት የተጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የማክሮ ኢኮኖሚውን በማረጋጋትና በማጠናከር፣ የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ፣ የፋይናንስ ስርዓቱን በማዘመን እና ኢንቨስትመንት በመሳብ ውጤቶች ተገኝተውበታል ብለዋል።
የዳንጎቴ ፔትሮሊየም እና ፔትሮ ኬሚካል የመጀመሪያ አክሲዮን ሽያጭ መጀመር ባለሀብቶችን ለማፍራት እና ለታዳጊው የፋይናንስ ገበያ ትልቅ ዕድገት መሆኑንም ገልጸዋል።
ይሄውም የኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአፍሪካ ቢዝነሶች ከሀገር ውስጥ ባለፈ በጋራ ለመስራት ያለው አቅም እያደገ መምጣቱን ያሳያል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት ዕውን ለማድረግ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደጋፊ የገበያ መሠረተ ልማቶች መቋቋሙን ገልጸዋል።
እነዚህ ተቋማት የሀገር ውስጥ ካፒታል እንዲያሰባስቡ፣ አዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲፈጥሩ እና ዜጎች በኢኮኖሚ ዕድገቱ በቀጥታ እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የተለያየ የፋይናንስ ስርዓት መሰረት መጣላቸውን አስረድተዋል።
የአክሲዮን ሽያጩ በኢትዮጵያ የተመዘገበው የኢኮኖሚ መነቃቃት ማሳያ ሌላው ምዕራፍ መሆኑን ገልጸው፤ የአህጉሪቱ ኢኮኖሚ ዕጣ ፋንታ በራሷ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት፣ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንት መረብ እና ጥልቅ የኢኮኖሚ ውህደት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...
Sep 15, 2026