የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የወረዳው አርሶ አደሮች የውሃ አማራጮችን በመጠቀም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተሰማርተዋል

Nov 7, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሮቤ ፤ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡-በአካባቢያቸው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም የበጋ መስኖ ስንዴን እያለሙ መሆናቸውን የባሌ ዞን ጋሠራ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ልማት ከ183 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ከጋሠራ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል ሼህ አህመድ ከድር በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው የወንዝ ውሃን በሞተር ፓምፕ በመሳብ ባለፉት ሦስት ዓመታት ስንዴንና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬ በማፈራረቅ በማልማት ተጠቃሚ እየሆኑ ናቸው ።

ዘንድሮም አንድ ሄክታር መሬታቸውን በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ወደ ስራ መግባታቸውንና ከዚህም የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የዝናብ ወቅትን ብቻ በመጠበቅ ከሚያለሙት ሰብል የእለት ፍጆታቸውን መሸፈን እንዳልቻሉ ያስታወሱት ደግሞ ሌላው የወረዳው አርሶ አደር ከማል አብዱ ናቸው።

ባለፉት አመታት በተሰማሩበት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በመሰማራታቸው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ማደጉን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸው የሚገኘውን ወንዝ በሞተር ፓምፕ በመሳብ ከሌሎች የአካባቢያቸው አርሶ አደሮች ጋር በኩታገጠም አሰራር ስንዴንና ሌሎች ገቢ የሚያስገኙ ሰብሎችን እያለሙ መሆናቸውን አመልክተዋል።


የጋሠራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ተፈራ በበኩላቸው የወረዳው አርሶ አደር የዝናብ ውሃን ብቻ ጠብቆ ከሚያካሄደው የሰብል ልማት በተጓዳኝ በበጋውም ወቅት መስኖን በመጠቀም ስንዴንና ሌሎች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልይ መሐመድ በበኩላቸው በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ወቅት ከ183 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል ።

እስከ አሁን በተደረገው የሥራ እንቅስቃሴም ከ60 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ማልማት ተችሏል።

የበጋ መስኖ ስንዴን ውጤታማ ለማድረግ 2ሺህ የሚሆኑ የውኃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች በረዥም ጊዜ ብድር በልማቱ ለተሳተፉ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን እንዲሁ።

በዞኑ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ወቅት በተለያዩ ሰብሎችና አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ ከሚገኘው ከ183 ሺህ ሄክታር ከሚበልጥ መሬት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026