የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የሰሜን ወሎ አርሶ አደሮች በመኸር ወቅት ያለሙትን  ሰብል ፈጥነው በመሰብሰብ ወደ መስኖ ልማት ገብተዋል

Nov 24, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልዲያ፤ ሕዳር 13/2018(ኢዜአ)፡- በመኸር ወቅት አልምተው የደረሰውን ሰብላቸው ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ለመጠበቅ ፈጥነው በመሰብሰብ ወደ መስኖ ልማት መግባታቸውን በሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

በሰሜን ወሎ ዞን በተያዘው የበጋ ወቅት 14 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ወደ ተግባር መገባቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገልጿል።

አርሶ አደር ውበቱ አባተ በዘኑ የጉባላፍቶ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ባለፈው የመኸር ወቅት ያለሙትን የምግብ ሰብል ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ከወዲሁ ለመከላከል ቤተሰቦቻቸውን በማስተባበር ፈጥነው መሰብሰባቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ወደ መስኖ ልማት በመግባት ግማሽ ሄክታር የሚሆነውን መሬታቸውን በበጋ ስንዴ ዘር መሸፈናቸውን አስታውቀዋል።

ልማቱን እያከናወኑ ያሉትን የምርት ግብዓቶችንና የግብርና ባለሙያዎች ምክር በመጠቀም መሆኑን አንስተው፤ በዘር ከሸፈኑት 16 ኩንታል የስንዴ ምርት እንደሚጠብቁ አስረድተዋል።

አርሶ አደር ደሳለ ልሳነወርቅ በበኩላቸው የበጋ መስኖን በመጠቀም ግማሽ ሄክታር መሬት ላይ ሽንኩርትና ቲማቲም እያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህም በመኸር ወቅት አልምተው የደረሰውን ሰብል ፈጥነው በመሰብሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሽንኩርትና ቲማቲም ምርት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆኑን አርሶ አደሩ ጠቁመዋል።

በዞኑ ግብርና መምሪያ የመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ባለሙያ አቶ ወርቁ ደሳለ እንደገለጹት፤ በአካባቢው የበጋ መስኖ ልማት ላይ በማተኮር በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት እየተሰራ ነው።


እስካሁን 14 ሺህ 625 ሄክታር መሬት በማረስ 837 ሄክታር የሚሆነውን በስንዴ፣ ገብስ፣ ሽምብራና ሌሎች ሰብሎች መሸፈኑን ተናግረዋል።

አርሶ አደሮችን በማሳተፍ በሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር የበጋ መስኖ ልማት አንድ ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግም ማዳበሪያና የምርጥ ዘር ወቅቱን ጠብቆ የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በመኸሩ ወቅት ለምቶ የደረሰውን ሰብል ፈጥኖ በማንሳት የመስኖ ልማቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026